ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ነጻ ስልጠና ለወጣቶች

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ነጻ ስልጠና ለወጣቶች
ነጻ ስልጠና ለወጣቶች

ልዩ እድል የቆዳ እና የቆዳ ውጤቶችን ማምረት ላይ የራሳቸውን ቢዝነስ መጀመር ለሚፈልጉ አቃቂ ቃሊቲ ነዋሪ ለሆኑ ወጣቶች

ዱካ ዩዝ ሌድ ኦርጋናይዜሽን እና ሪዲም ዘ ጀነሬሽን ከአማኑኤል የልማት ድርጅት ጋር በመተባበር በማስተር ካርድ ፋውንዴሽን በተገኘ ድጋፍ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ለሚገኙ ወጣቶች “Windows of Hope” በተሰኘ ፕሮጀክት አማካኝነት የቆዳ እና የቆዳ ውጤቶችን ማምረት ላይ ስልጠና ሰጥጠው በዚሁ ዘርፍ ወጣቶች የራሳቸውን ስራ እንዲጀምሩ የማድረግ ስራ እየሰሩ ይገኛል።  
 
ይህ እድል በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ለሚገኙ እድሜአቸው ከ 18 እስከ 35 ላሉ ወጣቶች ሙሉ በሙሉ በነጻ የሚሰጥ ሲሆን፣ ከስልጠና ባለፈ የመስሪያ ቦታ ማመቻቸት፣ ተደራጅቶ ስራውን ለመጀመር የሚያስፈልጉ ፍቃዶችን፣ የመስሪያ ማሽኖችን እና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ለፕሮጀክቱ አባላት የሚያሟላ ነው።

🌟 የዚህ ፕሮጀክት አካል የሚሆኑ ወጣቶች በዋናነት ምን ያገኛሉ?

የህይወት ክህሎትና የስራ ፈጠራ (Entrepreneurship) ስልጠና
ተግባር-ተኮር የቆዳ እና የቆዳ ውጤቶችን የማምረት ስልጠና
እውቅና ያለው የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት (COC)
ስልጠናውን በተሳካ ሁኔታ ላጠናቀቁ ፍቃድ (ላይሰንስ) እንዲወጣላቸው እና የስራ ማሽን እንዲገዛላቸው በማድረግ ወደ ስራ የሚሰማሩበት ሙሉ ድጋፍ

👥 ማን መመዝገብ ይችላል?
▪️ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የነዋሪነት መታወቂያ ያላቸው
▪️ እድሜያቸው ከ18-35 ዓመት የሆኑ ወጣቶች
▪️ የሚሰጠውን ስልጠና ሙሉ በሙሉ ለመውሰድ ፍቃደኛ የሆኑ
▪️ የቆዳ እና የቆዳ ውጤቶችን ማምረት ላይ ለመማር ፍላጎት ያላቸው እና በዚሁ ዘርፍ ለመስራት ፍቃደኞች የሆኑ

📌 ስልጠናው የሚሰጥበት ቦታ:
አቃቂ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ

👥 ሴቶች፣ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች (IDPs)

ተዛማጅ ታሪኮች