ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ነጻ የትምህርት ዕድል ከሰዎች ለሰዎች ድርጅት

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ነጻ የትምህርት ዕድል ከሰዎች ለሰዎች ድርጅት
ነጻ የትምህርት ዕድል ከሰዎች ለሰዎች ድርጅት

በሰዎች ለሰዎች ድርጅት ወይንም Menschen für Menschen Foundation ስር የሚተዳደረው የሐረር አግሮ ቴክኒክና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ በ2019 የትምህርት ዘመን ብቁ የሆኑ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን በመጀመሪያ ዲግሪ መርሐግብር ምግብና መኝታን ጨምሮ ሙሉ ወጪያቸውን ሸፍኖ ማስተማር ይፈልጋል፡፡

የዚህ ዕድል ተጠቃሚ መሆን የምትፈልጉ ተማሪዎች ከነሃሴ 26 እስክ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ባሉት የስራ ቀናት በአካል በመቅረብና በድረ- ገጽ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን። ።

የመመዝገቢያ መስፈርቶች ፦ ትምህርት ሚኒስቴር በ2015፣ 2016፣ 2017 እና 2018 ዓ.ም. ያወጣውን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መስፈርት የሚያሟሉ፣ በ2015፣ 2016፣ 2017 እና 2018 ዓ.ም. የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ማካካሻ ፈተና(remedial exam) ያለፉ ተማሪዎች እና የደረጃ 4 የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ያጠናቀቁ፣ የCOC ፈተና ያለፉና ሁለት ዓመት እና ከዚያ በላይ የስራ ልምድ ያላቸው፡፡  
የምዝገባ ቦታዎች፡ በአዲስ አበባ ቦሌ ቡልቡላ በሚገኘው የሰዎች ለሰዎች ድርጅት ዋና መ/ቤት፤ ሐረር  በኮሌጁ ቅጥር ግቢ፤ የድርጅቱ ፕሮጄክት ጽ/ቤቶች በሚገኙባችው
በተጨማሪም በድረ-ገጻችን http://www.mfmattc.edu.et / ATTC telegram channel: https://t.me/ATTC_online ላይም መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር +251 966772012/0256664577/+251911386973 ወይም 0114714579 ደውሎ ማንጋገር ይቻላል፡፡ 
(ሰዎች ለሰዎች ድርጅት Menschen für Menschen Foundation)

ተዛማጅ ታሪኮች