ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ኢትዮጵያ 100 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያለው የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ተቋም ልታቋቁም ነው።

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ኢትዮጵያ 100 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያለው የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ተቋም ልታቋቁም ነው።
ኢትዮጵያ 100 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያለው የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ተቋም ልታቋቁም ነው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) በኢትዮጵያ የቤት መግዣ ብድር ፋይናንስን ለማስፋፋት የሚያስችል ታሪካዊ የትብብር ማዕቀፍ ዛሬ መፈራረማቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በ100 ቢሊዮን ብር ካፒታል የሚቋቋመው ተቋም፣ IFC እስከ 200 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ አስተዋጽኦ የሚያደርግበት እንደሚሆን አመልክተዋል።

ተቋሙ በባንክ ዘርፍ ያለውን የገንዘብ ፍሰት አለመመጣጠን ለመቅረፍ እና በመላ አገሪቱ ተደራሽ የሚሆን የቤት መግዣ ብድር ፋይናንስ የሚያስገኝ እንደሆነ ገልጸዋል።

በተጨማሪም አጋርነቱ በተመጣጣኝ ዋጋ 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለማቅረብ የተያዘውን ግብ ለማሳካት እና በፋይናንስ ስርዓቱ ውስጥ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማሳደግ የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት ወሳኝ እርምጃ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ፈጣን፣ ጠንካራና ሁሉንም ያካተተ ኢኮኖሚ መገንባቷን እንደምትቀጥል አስታውቀዋል።

#PMOEthiopia
ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች