አቢሲንያ ባንክ
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

አቢሲንያ ባንክ
ባንካችን በኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ በይፋ በመመዝገብ
አክሲዮኖችን ለገበያ አቀረበ
ባንካችን አቢሲንያ ዛሬ ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ በይፋ በመመዝገብ የጸደቁ 17,481,120 አክሲዮኖችን ለገበያ አቅርቧል።
በኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች
ገበያ አዳራሽ በተካሄደው በዚህ ዝግጅት ላይ የባንካችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ በቃሉ ዘለቀ በቅድሚያ የዝግጅቱን ታዳሚዎች እንኳን ወደዚህ ታሪካዊ ሁነት በሰላም መጣችሁ ካሉ በኋላ የአቢሲንያ ባንክ በኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮችገበያ መመዝገብ በባንካችን ታሪክ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ነው በማለት በአጽንኦት ተናግረዋል።
አቶ በቃሉ አያይዘው ይህ የዛሬው ወሳኝ ምዕራፍ ለባለአክሲዮኖቻችን የበለጠ ግልጽነትን፣ በካፒታል ገበያው ውስጥ ሰፊ ተሳትፎን እና ዘላቂ ዕሴት መፍጠርን የሚያጠናክር ጉልህ እርምጃ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚው በመጨረሻ ለኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን፣ ለኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ፣ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ ለማዕከላዊ የሰነድ ሙዓለ ንዋዮች ግምጃ ቤት (CSD) እንዲሁም ለሌሎች እገዛ ላደረጉ አካላት ሁሉ የላቀ ምስጋና አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ በበኩላቸው "የአቢሲንያ ባንክ የማኔጅመንት እና ቦርድ አባላት ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥታችሁና ከተቋማቱ ጋር በቅርበት ሰርታችሁ ለዚህ ስኬት በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ !"
ብለዋል።
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ጀነራል ሃና ተኸልቁ የባንካችንን አመራሮች እንዲሁም በዚህ ሂደት ውስጥ የተሳተፉትን ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ ካሉ በኋላ የካፒታል ገበያው አዲስ በመሆኑ ደንበኞች ይህን ገበያ እንዲያውቁት ማገዝ ይኖርብናል ሲሉ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ጥላሁን እስማኤል፣ የባንካችን የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ መኮንን ማንያዘዋል፣ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ ባለአክሲዮኖች፣ የሥራ አመራር አባላት፣የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች እና ሌሎች የተለያዩ ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች የዝግጅቱ ታዳሚዎች ነበሩ።