ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

አቢሲንያ ባንክ

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
አቢሲንያ ባንክ
አቢሲንያ ባንክ

ሐምሌ 27/2018 ኢትዮጵያ 805 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል አዲስ የዓለም አቀፍ ሥነ ምህዳር ጥበቃ ታሪክ ባስመዘገበችበት ማግስት ባንካችን አቢሲንያ በእንጦጦ - አካባቢ ከኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ተቋም ጋር በመቀናጀት የተለያዩ ሀገር በቀል ችግኞችን  ተከላ መርሐ-ግብር አካሄደ::

የባንካችን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች በዛሬው ዕለት ማለትም ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም እንጦጦ አካባቢ ልዩ ስሙ ፔንታጎን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ላይ የተለያዩ ሃገር በቀል ችግኞችን ተከሉ፡፡  የባንካችን ዋና ፋይናንስ ኦፊሰር የሆኑት አቶ አብረሃም ገበየሁ እንደገለፁት ባንካችን ማኅበራዊ ኃላፊነትን ከመወጣት አኳያ፤ እንዲሁም ፤ ችግኞች መተከላቸው ለአካባቢዊ ስነምህዳር ልማት፤ ንፁህ አየር ለመተንፈስና ለማግኘት፤ ብሎም (ESG) ከአካባቢያዊ፤ ማህበራዊ፤ እና ግልፅነት ለሰፈነበት አስተዳደራዊ አንዱ አካል መሆኑን በማውሳት ባንካችን አቢሲንያም የዚህ መርሃ ግብር ተሳታፊ  በመሆኑ፤ በተጨማሪም ልክ እንደ አንዱ የባንኩ እሴትም የተከልናቸውን ችግኞች መንከባከብ(Caring)፤ መጠበቅ አንዱ አካል በመሆኑ በባንኩ ስም በዕጅጉ ደስተኛ መሆናቸውን በማውሳት በቀጣይም መሰል አካባቢያዊ ልማት ላይ በሰፊው እንደሚሳተፍ አውስተዋል፡፡

በመቀጠልም ከኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ  ተቋምን በመወከል አቶ ሰለሞን ስዩም - የማርኬቲንግ እና ኮምዩኒኬሽን ሃላፊ የሆኑት አቢሲንያ ባንክ ባሳለፍነው በጀት ዓመት ላስመዘገበው ከፍተኛ ውጤት ለባንኩ የቦርድ አባላትና ለባንኩ ሰራተኞች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ውጤታችሁ የጠንካራ አመራር ፤ የትጋት፤ የታማኝነትና እና የቡድን ስራ ውጤት በመሆኑ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ  ዛሬ ፤ ይህም የተፈጥሮን ሀብት መጠበቅና ለመጪው ትውልድ አረንጓዴ ቅርስ ማኖር ነው።

የዛሬው መርሃ ግብር የዛፍ ተከላ ብቻ ሳይሆን ለሀገራችን ተፈጥሯዊ ስነ ምህዳር ብሎም ለመጪው ትውልድ ውርስና ቅርስ የምናቆይበት ሁነትም ጭምር መሆኑን በማውሳት፤ አቢሲንያ ባንክ በዲጂታልና በቨርቹዋል የባንክ አገልግሎት ፈር ቀዳጅ ከሆኑ የኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት አንዱ ሲሆን ደንበኞቹን በቴክኖሎጂ ወደፊት እንዲራመዱ እንዳደረገ ሁሉ፣ ዛሬም ተፈጥሮን በመመለስና በማገገም ሂደት ውስጥ ፈጣን ምላሽ ከሚሰጡ ተቋማት ግንባር ቀደም መሆኑን እያረጋገጠ መሆኑን በተግባር ያሳየY ሲሆን ፤ የፋይናንስ ሒደትን ከአካባቢ ጥበቃ ጋር ማጣመር የዘመናዊ ተቋማት መለያ ነው፤ ካሉ በኋላ  አቢሲንያ ባንክም ይህንን በተግባር እያሳየ እንደሚገኝ በመግለፅ ኢኮኖሚና ተፈጥሯዊ ሥነ-ምህዳር የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች በመሆናቸው የተፈጥሮ ሀብታችንን ካጠፋን ኢኮኖሚያችንን እንጎዳለን፤ ሥነ-ምህዳራችንን ካለማን ደግሞ የዘላቂ ልማት መሠረት እንጥላለን። ስለዚህ የዛሬው የዛፍ ተከላ በእርግጥ ለኢኮኖሚያችንም የምናደርገው ኢንቨስትመንት መሆኑን በመጥቀስ ለባንኩ ያላቸውን ምስጋና ገልጸዋል፡፡

በችግኝ ተከላ መርሃ - ግብሩ ላይ የባንካችን ከፍተና የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች እንዲሁም የቅርስ ባለአደራ የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም ከተለያዩ የስራ ክፍሎች የተውጣጡ የባንካችን ሰራተኞች  የተገኙ ሲሆን ባንኩ ወደፊትም መሰል ተግባራትን አጠናክሮ እንደሚቀጥል በዕለቱ ተገልጿል፡፡

ተዛማጅ ታሪኮች