ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

" እነ ክርስቲያን ተፈተዋል " - የአቶ ክርስቲያን የቅርብ ቤተሰብ

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
" እነ ክርስቲያን ተፈተዋል " - የአቶ ክርስቲያን የቅርብ ቤተሰብ
" እነ ክርስቲያን ተፈተዋል " - የአቶ ክርስቲያን የቅርብ ቤተሰብ

እነ አቶ ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ ሌሎች እስረኞች ከእስር መፈታታቸውን፣ እነ አቶ ዮሐንስ ቧያሌውና ሌሎች የይቅርታ ፎርም ያልሞሉት እንዳልተፈቱ ቤተሰቦቻቸው ተናገሩ።

የአቶ ክርስቲያን ታደለ የቅርብ ቤተሰብ አቶ ክርስቲያን ጨምሮ 600 እስረኞች ዛሬ ከእስር መፈታታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የአቶ ዮሐንስ ቧያሌው የቅርብ ቤተሰብ በበኩላቸው፣ እነክርስቲያን ታደለን ጨምሮ ሌሎችም ዛሬ ከእስር መፈታታቸውን ነግረውናል።

አቶ ዮሐንስ ቧያሌው ከእስራት እንዳልተፈቱ ገልጸው፣ " የተፈቱት ከመንግስት ጋር ተስማምተው የይቅርታ ፎርም የሞሉት ናቸው። ያልፈረሙት ጋር አዲስ ነገር የለም " ሲሉም አክለው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

በተጨማሪ፣ ሌላኛው እስረኞቹ ቅድመ ሁኔታዎች ላይ ፈርመው በይቅርታ እንዲፈቱ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኩል ተይዞ የነበረውን ጉዳይ እየተከታተሉ የነበሩ አካል በበኩላቸው፣ የቀረበው ቅድመ ሁኔታ ላይ የፈረሙት እስረኞች " ተፈትተዋል " ፣ ያልፈረሙት " አልተፈቱም " በማለት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ስነዱ ላይ ሳይፈርሙ ሳይፈተ ከእስር ያልተፈቱት ወደ 28 የሚጠጉ ናቸው።

ከ600 በላይ እስረኞች ተፈቱ የሚለውን በተመለከተ፣ " ልክ ነው፤ እኛ የአማራ ፖለቲከኞችን ነው የምናውቀው። ግን የኦሮሚያ ፖለቲከኞችም አሉ። የሌሎች ብሔሮችም ይኖራሉ። የትግራም አሉ የሚባል ነገር አለ። እንደዛ አይነት መረጃ አለኝ " ሲሉም ነግረውናል።

እስረኞቹ ቅድመ ሁኔታ ላይ ከፈረሙ ከእስር እንዲፈቱ ካልፈረሙ ደግሞ እንዳይፈቱ መደረጉ ከፍርድ ሂደቱ ጋር ያለውን ሁኔታ ሲያስረዱ፣ በፍርድ ስርዓቱ " አፋጣኝ ፍትህ ማገኘት ነበረባቸው " ይላሉ።

" በፓርላማ በተለያየ ጊዜ የተነገረ ጉዳይ ነው። የፍትሕ ሚኒስቴር አንዱ ተልዕኮ አስቸኳይ ፍትህ ማስፈን ነው፤ ግን በጣም ችግር እንዳለበት፤ ባለፉት አመታት አንድም አሳማኝ መረጃ ሳይገኝባቸው ለምንድነው  ፍትህ ሚኒስቴር ክሱን የማያቋርጠው ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

" እንደዚያ ነበር መሆን ያለበት፣ የፍትህ ስርዓቱማ ችግር እንዳለበት ሁሌም የምንናገረው ነገር ነው " ያሉት እኚሁ አካል፣ " መታሰብ ያለበት ደግሞ ጦርነት ላይ ነን ፤ ገዥው ፓርቲ ከታጣቂ ቡድኖች ጋር። ስለዚህ እውነተኛ ፍትህ መጠበቅ የማይሆን ነገር ነው " ይላሉ።

" ከዚህ በኋላ እነዚህ ሰዎች በእስር ቢቆዩ እንዴት አድርገው ነው የፍትህ ስርዓቱን የሚያሻሽሉት ? በፍፁም ሊያሻሽሉት አይችሉም። ጦርነት ላይ ሁነህ አይሆንም " ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

" ከተቃዋሚ ጎራ ያለውም የሆነ የራሱ ጥፋት ይኖረዋል፤ ገዢው ፓርቲም ጥፋት ይኖረዋል። ወንጀሎች ከሁለቱም ወገን የመፈጠር እድል አላቸው። መንግስት ደግሞ ጦርነት ላይ 'ማስረጃ ተደብቆ ነው እንጂ እነዚህ ሰዎች አጥፍተዋል፤ ማረጃ ለጊዜው ስላላገኘው ነው ጊዜ ይሰጠኝ ' እያለ እያራዘመ ለዘመናት ያስራቸዋል " ብለዋል።

" በመሆኑም እስረኞቹ በይቅርታ እንዲፈቱ ቅድመ ሁኔታ ተቀምጦላቸው ' ይፈቱ፣ አይፈቱ ' ከሚባል ይልቅ በፍትህ ሂደቱ እንዲፈቱ መሆን ይችል የነበረው አገር በተረጋጋችበት ሁኔታ፣ መንግስት የፍትህ ስርዓቱ ለማዘመን ጥረት እያደረገ እያለ ባለበት ቢሆን ነው " የሚል አስተያየት ሰጥተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ጳጉሜን 5 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች