እናት ባንክ የGlobal Alliance for Banking onValues (GABV)የአፍሪካ ቀጠና ስብሰባ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ አስተናገደ።
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

እናት ባንክ የGlobal Alliance for Banking onValues (GABV)የአፍሪካ ቀጠና ስብሰባ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ አስተናገደ።
እናት ባንክ የአለም አቀፍ እሴት ተኮር ባንኮች ህብረት (GABV) የአፍሪካ ቀጠና ስብሰባን በአዲስ አበባ ሀያት ሪጀንሲ ሆቴል በይፋ ማስጀመሩን ገለጸ። እስከ ጥቅምት 22 ቀን 2026 የሚቀጥለው ይህ ታሪካዊ ጉባኤ የቀጠናውን እና የአለም አቀፍ እሴት መር ባንክ መሪዎችን በጥቅል ያስተባበረ ሲሆን፣ የጉባኤው መሪ ቃልም፦ "የባንክ አገልግሎትን ማሻሻል፦ አካባቢያዊ፣ ማህበራዊ እና አስተዳደራዊ እና ቴክኖሎጂን ለፋይናንስ ተፅዕኖ መጠቀም" የሚል ነው።
የእናት ባንክ የቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሮ አስቴር ሰለሞን በመክፈቻ ንግግራቸው፤ ባንኩ ሴቶችንና ቤተሰቦቻቸውን በኢኮኖሚ የማብቃት እንዲሁም ለመላው ህብረተሰብ አጠቃላይና ተደራሽ የባንክ አገልግሎት የመስጠት ራዕይን ሰንቆ የተመሰረተ መሆኑን አብራርተዋል።
ወይዘሮ አስቴር አክለውም፤ እናት ባንክ ለፈጠራ፣ ለአካታችነት፣ ለዘላቂነት እና ለኢንቨስትመንት እድሎች በሰጠው ትኩረት አወንታዊ የፋይናንስ ውጤቶችን ማስመዝገቡን፣ ስልታዊ የንግድ አጋርነቶችን መገንባቱን እና ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት ቀጥተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልጸዋል።
በተጨማሪም በስርዓተ-ፆታ ፋይናንስ ዘርፍ የተመዘገቡ ዋና ዋና ስኬቶችን ጠቅሰዋል፦
እ.ኤ.አ. 2025፦ የስርዓተ-ፆታ ፋይናንስ አካታችነትን በማሳደግ በ "Gender Scorecard" ብቸኛው "ትራንስፎርሜሽናል ባንክ" በመባል እውቅና አግኝቷል።
እ.ኤ.አ. 2026፦ የሴቶችን የፋይናንስ ተደራሽነት በማስፋፋት ረገድ የ "ገበያ መሪ" (Market Leader) ክብር ተሰጥቶታል። እናት ባንክ ለህብረተሰቡ አጠቃላይ የፋይናንስ ተደራሽነትን የበለጠ ለማስፋት ታሪካዊ የሆነውን የ "Gender Bond" (የስርዓተ-ፆታ ቦንድ) ለመጀመር ዝግጅቱን አጠናቋል።
ወይዘሮ አስቴር አክለውም "እናት ባንክ ከ GABV ጋር በሚያደርገው ንቁ ተሳትፎና ትብብር ዘላቂ እሴት እንደሚፈጥር በተግባር ተገንዝቧል" ብለዋል።
የ GABV ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማርቲን ሮህነር በበኩላቸው፤ ጉባኤው አባላት የፈጠራ ሃሳቦችን እንዲያመነጩ፣ የዘርፍ ልምዶችን እንዲለዋወጡ እና የባንክ ዘርፉን ለማሻሻል በጋራ እንዲሰሩ እድል እንደሚፈጥር አብራርተዋል። እናት ባንክ የ 2026 የ GABV የአፍሪካ ቀጠና ስብሰባን በማስተናገዱና በዘላቂ ፋይናንስ ላሳየው አመራር ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ (NBE) የባንክ ሱፐርቪዥን ዳይሬክተር አቶ ፍሬዘር ያለው በበኩላቸው፤ የሀገር ውስጥ የባንክ ዘርፍ ወደ ዲጂታል አገልግሎቶችና አካታች ፋይናንስ ያደረገው ትኩረት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እድገት እና መነቃቃት እያሳየ መሆኑን ገልጸዋል። ከስብሰባው የሚገኙ መልካም ተሞክሮዎች የኢትዮጵያን የፋይናንስ ተቋማት ሙሉ ውጤታማነትና ጥንካሬ ለማሳደግ እንደሚረዱ አክለው ገልጸዋል።
ማን እንደ እናት!