" ወደ ተለያዩ ቦታዎች ለመሄድ መናኸሪያ ላይ ተሰብስበው የነበሩ 18 ንጹሐን ተገድለዋል " - አቶ ለሜሳ ኔኖ
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

" ወደ ተለያዩ ቦታዎች ለመሄድ መናኸሪያ ላይ ተሰብስበው የነበሩ 18 ንጹሐን ተገድለዋል " - አቶ ለሜሳ ኔኖ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን፣ ግልገል በለስ ከተማ ታጣቂዎች በከተማዋ መናኸሪያ አካባቢ በከፈቱት ተኩስ 18 ሰዎች መገደላቸውንና ሌሎች መቁሰላቸውን ነዋሪዎችና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አባል አቶ ለሜሳ ኔኖ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
አቶ ለሜሳ እንደገለጹት፣ ጥቃቱ ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ከንጋቱ 12 ሰዓት አካባቢ ተፈጽሟል።
መኩሪያ በተባለ ግለሰብ የሚመራ ታጣቂ ቡድን ወደ ግልገል በለስ ከተማ በመግባት ድንገተኛ ተኩስ እንደከፈተ ገልጸዋል።
" ከዚህ በፊት ከሰላም ጥሪ አፈንግጦ የተመለሰው መኩሪያ በተባለ ሰው የሚመራ ታጣቂ ቡድን ነው ጥቃቱን የፈጸመው። ብዙ ጊዜ ጥሪ ተደርጎ የመምጣት ፍላጎት አልበረውም " ብለዋል።
ዛሬ ጥዋት ወደ ተለያዩ አቅጣጫዎች ለመጓዝ መናኸሪያ ላይ ተሰብስበው የነበሩ ተሳፋሪዎች በተኩሱ ሰለባ መሆናቸውን አቶ ለሜሳ ገልጸው፣ ወደ 18 የሚጠጉ ንጹሐን መገደላቸውን ተናግረዋል።
በተጨማሪም ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች መቁሰላቸውንና ለሕክምና ወደ ጤና ተቋማት መወሰዳቸውን ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው የመተከል ዞን ነዋሪዎች በግልገል በለስ ከተማ በዚያ ጠዋት ከባድ ተኩስ ተከፍቶ ሰዎች መሞታቸውን አመልክተዋል።
አንድ ነዋሪ መናኸሪያ ላይ በተከፈተ ተኩስ በመጀመሪያ ስምንት ሰዎች መገደላቸውንና ሁለት ሰዎች ከባድ ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል። በኋላ በደረሳቸው መረጃ የሟቾች ቁጥር 18 መድረሱን ተናግረዋል።
ሌላኛው ነዋሪ የ " ጉሙዝ ታጣቂዎች " ንጋት 12:00 አንስቶ በከፈቱት ተኩስ የሰው ህይወት ማለፉን አመልክተዋል።
ሶስተኛው ነዋሪና የመረጃ ምንጭ ደግሞ፣ በግልገል በለስ መናኸሪያ አካባቢ በተከፈተው የከባድ መሳሪያ ተኩስ የሰው ህይወት ማለፉንና ሰዎች መጎዳታቸውን ገልጸዋል። ከዚህ በተጨማሪ አንድ ቤተክርስቲያን የሚገኝበት አካባቢ ላይም ጥቃት መፈጸሙን ጠቁመዋል። " ከተማዋን ለመቆጣጠር የሞከሩት የጉምዝ ታጣቂዎችን እና ፋኖ በጋራ በመሆን ነው " ብለዋል።
ፖሊስ ምን አለ ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለተኩሱ ማብራሪያ የጠየቃቸው አንድ የከተማዋ ፖሊስ አካል፣ " ሰላም ነው፤ ምንም ነገር የለም አሁን " ብለዋል።
" በዚህ ሰዓት ሚዲያ ይጠይቃል እንዴ? " ሲሉ ጠይቀው፣ ተጨማሪ ማብራሪያ ከመስጠት በመቆጠብ ስልክ ዘግተዋል።
የመተከል ዞን አስተዳደር ምን አለ ?
የመተከል ዞን አስተዳደር በጉዳዩ ላይ ባወጣው መግለጫ የሟቾችን ወይም የቆሰሉትን ቁጥር አልጠቀሰም።
ነገር ግን “የጉሙዝ ኃይል” ብለው የሚጠሩ በጫካ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ከፋኖ ጋር በመሆን ወደ ግልገል በለስ ከተማ ለመግባትና በዜጎች ላይ ጉዳት ለማድረስ ሙከራ ማድረጋቸውን ገልጿል።
የዞኑ አስተዳደር እንዳለው፣ የፀጥታ ኃይሎች ባደረጉት የተቀናጀ እርምጃ የታጣቂዎቹ ሙከራ መክሸፉንና ታጣቂዎቹ ከከተማዋ መመለሳቸውን ገልጿል።
አሁንም በከተማዋ ሰላምና መረጋጋት መኖሩን እና የፀጥታ ኃይሎች ዝግጅታቸውን አጠናክረው መቀጠላቸውን አስታውቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia