ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

" የማህበራዊ ሚዲያ አጠቀማችሁን በማስተካከል የአእምሮ ጤናችሁን ጠብቁ " - ዶ/ር መገርሳ አለሙ

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
" የማህበራዊ ሚዲያ አጠቀማችሁን በማስተካከል የአእምሮ ጤናችሁን ጠብቁ " - ዶ/ር መገርሳ አለሙ
" የማህበራዊ ሚዲያ አጠቀማችሁን በማስተካከል የአእምሮ ጤናችሁን ጠብቁ " - ዶ/ር መገርሳ አለሙ

ከሰሞኑን ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የአእምሮ ጤና ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዶ ነበር።

በዚህም መድረክ የህመም ደረጃው ቢለያይም በኢትዮጵያ ከ5 ሰዎች አንዱ የአእምሮ ጤና ችግር እንዳለበት ጥናቶች ያሳያሉ ተብሏል።

የሆስፒታል ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር መገርሳ አለሙ፤
- በቀላሉ መበሳጨት፣
- ተደጋጋሚ ድብርት፣
- መነሻ የሌለው ፍርሃት እና ሌሎች ስሜቶችን ሰዎች በቀላሉ የሚያልፏቸው ቢሆንም የአእምሮ ጤና ችግር መነሻ ሊሆኑ ይችላሉ ብለዋል።

በዚህ ባለንበት የድጅታሉ ዘመን ፦
° የምንስማቸው አስፈሪ እና ዘግናኝ ወሬዎች፣
° ጦርነት፣
° መፈናቀል እና ሞቶች ሰዎችን ከቀላል እስከ ከባድ የአእምሮ ህመም የማጋለጥ ዕድላቸው ሰፊ መሆኑን አስረድተዋል።

አብዛኛው ሰው በከፍተኛ የህመም ደረጃ ካልደረሰ በቀር የአእምሮ ህመም ታማሚ መሆንኑ እንደማያውቅ ተመላክቷል።

የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም በማስተካከል፣ በተቻለ መጠን ጭንቀት፣ ድባቴ እና ፍርሃት ከሚፈጥሩ ወሬዎች በመራቅ ሰዎች የአእምሮ ጤናቸውን እንዲጠብቁ መክረዋል።

" ጥቃቅን የሚመስሉ ስሜቶችንም አቅልሎ ማየት አያስፈልግም " ሲሉ አሳስበዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

ነሐሴ 15 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች