ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

#የትርፍሰዓትክፍያ

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
#የትርፍሰዓትክፍያ
#የትርፍሰዓትክፍያ

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ የጤና ባለሙያዎችን የትርፍ ሰዓት (ዱቲ) ውዝፍ ክፍያ ወደ ኋላ ተመልሶ እንደማይከፈል መናገሩን የጤና ባለሙያዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

ከሰሞኑን ከተቋማት ኃላፊዎች ጋር በነበረ አንድ ስብስባ ላይ የቢሮው ከፍተኛ አመራር " እስከ ሀምሌ 1/2018 ዓ.ም ድረስ የሰሩበትን የትርፍ ሰዓት (ዱቲ) ውዝፍ ክፍያ ወደ ኋላ ተመልሶ ክፍያ እንደማይፈጽም " መናገራቸውን ከድምጽ ማስረጃ ጋር አድርገው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ልከዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባዳመጠው የድምጽ ፋይል ላይ፣ አመራሩ አሁን ላይ ወጥቷል ባሉት አዲስ የትርፍ ሰዓት ክፍያ መመሪያ መሰረት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ከሀምሌ 1/2018 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል።

አመራሩ " ሆስፒታሎች ባለሙያዎችን ብዙ ሳታጉላሉ ክፈሉ ፤እኛ በጀት ይዘናል "  ሲሉ ተደምጠዋል።

የክልሉ የጤና መምሪያዎች የቅድመ-ወጪ ስሌታቸውን እንዲያቀርቡም የተጠየቁ ሲሆን፣ ሆስፒታሎችም የቀደመውን የትርፍ ሰዓት ክፍያ ሳይነኩ የዱቲ ክፍያን በተሰጠው ግልጽ የሒሳብ ስሌት መመሪያ መሠረት ብቻ እንዲፈጽሙ ኃላፊው አሳስበዋል።

" አሁን በጸደቀው መመሪያ ከዚህ በኋላ ያለውን ነው እንድከፈል የሚያዘው " ያሉት አመራሩ " ወደኋላ ያለ የዱቲ ክፍያ የለንም፤ ውዝፍ ክፍያ (backlog) የሚባል ነገር የለም። በነበረው ደሞዝ፣ በተበጀተው በጀት ነው ክፈሉ ያልናችሁ። የድጎማ በጀት እናገኛለን ብለን ከክልል እስከ ፌዴራል ሄደናል፤ የበጀት እጥረት ስላለ ድጎማ የለም " ብለዋል።

" የትርፍ ሰዓት ክፍያ የሰጣችሁትን ሰው አንነካም። የተከሰሰ ሰው ካለ ' እኔ በተመደበልኝ በጀት ይህንን ከፍያለሁ፤ የበጀት ስርጭቱ ላይ አልተካተተም ' ብላችሁ መልሱ ከዚያ የሚሆነውን አብረን እናየዋለን፣ ምክንያቱም የክልሉ በጀት ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።

" 3.7 ቢሊዮን ብር ለሆስፒታል፣ 5.3 ቢሊዮን ለጤና ጣቢያ ከሀምሌ 1/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለትርፍ ሰዓት ክፍያ የሚውል በጀት አስፈቅደናል " ሲሉ አሳውቀዋል።

አመራሩ፣ " ለዱቲ ክፍያ የሚሆን 8.9 ቢሊዮን ብር ከራሳቸው ከተቋማቱ የውስጥ ገቢ የሚሸፈን ሆኖ፣ በCGS በኩል የቅድመ-ወጪ ግምት ተሰርቶለት በጀት ሆኖ ተይዟል፤ በአንዳንድ ሁኔታዎች ላይ ተመስርተን መደራደር ያስፈልጋል " ብለዋል።

" እኛ ስለተፈቀደልን ይሄንን እናስቀጥላለን፤ እናንተ መረጃ (ዳታ) ላይ ተመስርታችሁ ውሳኔ እየሰጣችሁ ሂዱ፤ በተቻለ መጠን ሥራዎቹን በዚያ መሠረት ለማስቀጠል እንሄዳለን እንጂ በትርፍ ሰዓት ክፍያ ሰበብ አድርጎ ሌሎች ሥራዎችን ማስተጓጎል አይቻልም " ሲሉ የጤና ተቋማት ኃላፊዎችን አስጠንቅቀዋል።

አመራሩ፣ " ማንኛውም የዱቲ ክፍያ የሚፈጸመው በየክፍሉ (ዲፓርትመንት) የተከናወኑ የሌሊትና የትርፍ ሰዓት ሥራዎች በፋይናንስ ቡድንና በኃላፊዎች ተመዝግበው ሪፖርት ሲደረጉ ይሆናል " ብለዋል።

" የክፍያ ስሌት ከባለሙያ ብዛት ይልቅ ትክክለኛውን የሕክምና አገልግሎት በመቁጠር የሚከናወን ነው። የትኛው ባለሙያ ምን ዓይነት አገልግሎት እንደሰጠ ግልጽ ያደርጋል " ሲሉ አክለዋል።

"​ የባለሙያዎች የሥራ ስብጥር (ሬሾ) እና ክፍያ እንደ ተቋማቱ ደረጃ (ኮምፕሬንሲቭ፣ ጄነራል፣ ፕራይመሪ) እና እንደ ክፍሎቹ የስጋት ደረጃ (Risk) ተለይቶ ይሰላል። ተግተው የሚሰሩ እና አሰራር የሚያጭበረብሩ ባለሙያዎችን በዳታ ለይቶ የማስተካከያ እርምጃ ይወሰዳል " ሲሉ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች