ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ለአባይ ቴሌቪዥን ማስጠንቀቂያ ሰጠ፤ ጣቢያውም ይቅርታ ጠይቋል።

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ለአባይ ቴሌቪዥን ማስጠንቀቂያ ሰጠ፤ ጣቢያውም ይቅርታ ጠይቋል።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ለአባይ ቴሌቪዥን ማስጠንቀቂያ ሰጠ፤ ጣቢያውም ይቅርታ ጠይቋል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን አባይ ቴሌቪዥን ባለፉት ሦስት ወራት ባሰራጫቸው ዜናዎች፣ ፕሮግራሞችና ማስታወቂያዎች ላይ የተስተዋሉ የሕግና የጋዜጠኝነት ሙያ ሥነ-ምግባር ጥሰቶችን በመመርመር ለጣቢያው ማስጠንቀቂያ ሰጠ።

ባለሥልጣኑ ከሰኔ እስከ ነሐሴ 2018 ዓ.ም. ባካሄደው የሚዲያ ይዘት ክትትል፦

- ከማኅበረሰቡ ባህል፣ ወግና እሴት የሚጋጩ ፀያፍ ንግግሮችና አባባሎች መሰራጨታቸው፤

- በወጣቶች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ይዘቶች መቅረባቸው፤

- የሴቶችን ክብር የሚነኩ ይዘቶች መስተዋላቸው፤

- በአንዳንድ ዜናዎች ያልተረጋገጡ ምንጮች መጠቀማቸው ፤ ... እንደ ዋና ጉድለቶች መጠቀሳቸውን ገልጿል።

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኃይማኖት ዘለቀ እነዚህ ጥሰቶች በምንም መልኩ ተቀባይነት የሌላቸው በመሆናቸው ፈጣን የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ አሳስበዋል።

በተጨማሪም ጣቢያው የአገሪቱን ሕጎች፣ የመገናኛ ብዙኃን አዋጅና የጋዜጠኝነት ሙያ ሥነ-ምግባርን ከኤዲቶሪያል ፖሊሲው ጋር በማጣጣም በጥንቃቄ እንዲተገብር አስገብዝበዋል።

የአባይ ቴሌቪዥን ኃላፊዎች በበኩላቸው በክትትሉ የተጠቆሙትን ጉድለቶች ተቀብለው፣ ለተፈጠሩት ስህተቶች ይቅርታ ጠይቀዋል። በተጨማሪም የተሰጡትን ምክረ ሐሳቦች በመተግበር የጣቢያውን የይዘት ጥራት ለማሻሻል እንደሚሠሩ ገልጸዋል።

ምንጭ፦ https://www.facebook.com/share/1EVB1jeb4G/

ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች