የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) 5ኛውን የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ ቻሌንጅ ፕሮግራም አስጀምሯል።
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) 5ኛውን የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ ቻሌንጅ ፕሮግራም አስጀምሯል።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) በሃገር በቀል ቴክኖሎጂዎች የሃገርን መሰረተ ልማቶች የሚጠብቅ "ዲጂታል ሰራዊት" ለመገንባት ያለመውን 5ኛውን ዙር ብሔራዊ የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ (Cyber Talent Summer Camp Challenge) ፕሮግራም በአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አስጀምሯል።
አስተዳደሩ ባለፉት አራት ተከታታይ ዓመታት ሲያካሂደው የቆየው ይህ ፕሮግራም፣ የሀገሪቱን የሳይበር ደህንነትና ሉዓላዊነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ እንዲሁም በ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ስትራቴጂ የተቀመጡ ግቦችን በማሳካት በዘርፉ ብቁ የሆኑ "የዲጂታል ሰራዊት" ወጣቶችን ለማፍራት ያለመ መሆኑ ገልጿል።
ስልጠናው ከአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በተጨማሪ በባህር ዳር ፣ ደብረ ብርሃን ፣ ወላይታ ሶዶ ፣ ሐረማያ እና ጅማ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም በኢመደአ ታለንት ማዕከል ይሰጣል ።
በአጠቃላይ በሰባት የስልጠና ማዕከላት የሚሰጠው ይህ ፕሮግራም 1ሺ 249 ተማሪዎች ለአንድ ወር ስልጠናቸውን እየተከታተሉ የሚቆዩ ይሆናል።
ስልጠናው :-
• ሳይበር ደህንነት (Cyber Security)
• ሶፍትዌር ዴቨሎፕመንት(Software Developmet)
• ኤምቤድድ ሲስተም (Embedded System)
• ኤሮስፔስ (Aerospace)
• ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ (Emerging Technology) ዘርፎችን ያካተተ ነው።
በቆይታቸው የአካል ብቃት ፣ የስነልቦና ድጋፎችን እና ቼዝን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ተከታታይ የሆኑ ስልጠናዎችን የሚሰጣቸው ሲሆን በማብቂያው ላይም ፕሮጀክቶችን የሚሰሩ ይሆናል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia