ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት 11 ተጨማሪ የሥልጠና ዘርፎችን በማካተት ምዝገባ እያከናወነ መሆኑን ገለጸ።

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት 11 ተጨማሪ የሥልጠና ዘርፎችን በማካተት ምዝገባ እያከናወነ መሆኑን ገለጸ።
የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት 11 ተጨማሪ የሥልጠና ዘርፎችን በማካተት ምዝገባ እያከናወነ መሆኑን ገለጸ።

👉 የተቋሙን መስፈርት የሚያሟሉ የመደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ እስከ መስከረም 25/2019 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል።

የፌዴራል የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት የዘመኑንና የወደፊቱን የገበያ ፍላጎት ያማከሉ ናቸው ያላቸውን አዳዲስ የሥልጠና መስኮችን በማካተት የተማሪዎች ምዝገባ እያከናወነ እንደሚገኝ ገለጸ።

ኢንስቲትዩት እነዚህን ተጨማሪ የስልጠና መስኮች ያስተዋወቀው ከመስከረም 14/2019 ዓም ጀምሮ ክፍት የሚሆን የመረጃ ሳምንትን ይፋ ባደረገበት መርሃ ግብር ላይ ነው።

ተቋሙ ላለፉት ከ15 ዓመታት በላይ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ብቸኛው ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት

• በመጀመሪያ ዲግሪ (ደረጃ 6) በ29 ፕሮግራሞች፣

• በሁለተኛ ዲግሪ (ደረጃ 7) በ23 ፕሮግራሞች እንዲሁም 

• በሦስተኛ ዲግሪ (ደረጃ 8 / ፒኤች.ዲ) በ2 ፕሮግራሞች ሥልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።

በተለይም በ2018 ዓ.ም ደግሞ የዓለም ገበያ የክህሎት ፍላጎትን ያገናዘቡ ናቸው የተባሉትን 11 መስኮች ማለትም :-

- ባዮሜዲካል ቴክኖሎጂ፣
- የሳይበር ደህንነት፣
- አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI)፣
- ኢንተለጀንት ሮቦቲክስ፣
- ፕላስቲክ ቴክኖሎጂ
- ሆርቲካልቸር
- ኢንቴሪየር ዲዛይን እና ፊኒሺንግ
- ሌዘር ፕሮዳክት
- በTVET ሊደርሺፕ እና ማኔጅመንት
- በማኑፋክቸሪንግ
- ፋሽን ዲዛይን እና በአዳዲስ ኢነርጂ ተሽከርካሪዎች ቴክኖሎጂ ዘርፍ የፈጠራና የወደፊት የሥልጠና መስኮች (Emerging Skills) ተቀርጸው ወደ ተግባር መግባታቸው ተገልጿል።

ሥልጠናው 50 በመቶ የንድፈ-ሀሳብ እና 50 በመቶ የተግባር ልምምድ እንዲሆን በተሟሉ ወርክሾፖች የተደገፈ ነው የተባለ ሲሆን ተቋሙ በ16 ሳተላይት ካምፓሶችና በ2 ማዕከላት አማካኝነት ከ 10 ሺ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ዝግጁ መሆኑን አሳውቋል።

ኢንስቲትዩቱ ከቻይና እና አልጄሪያ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በጥምረት የዲግሪ ፕሮግራሞችን ከመስጠት ባሻገር፣ በየዓመቱ ከ300 በላይ ለሚሆኑ የደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ እና ሌሎች የጎረቤት ሀገራት ዜጎች ነፃ የሥልጠና ዕድል እየሰጠ መሆኑን አሳውቋል።

የተቋሙን መስፈርት የሚያሟሉ የመደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ እስከ መስከረም 25/2019 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይ የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት ይፋ አድርጓል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች