" ጎንደር ኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት ወደ 84 አካባቢ ክፍሎች አሉት " - አቶ ጋዲሳ ግርማ
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

" ጎንደር ኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት ወደ 84 አካባቢ ክፍሎች አሉት " - አቶ ጋዲሳ ግርማ
በአማራ ክልል፣ ጎንደር ከተማ እየተገነባ ያለውና ወደ መጠናቀቅ የደረሰው የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት ግንባታ " ጥሩ እየሄደ " መሆኑንና በቀጣዩቹ ሁለት፣ ሦስት ወራት ወደ ሥራ እንደሚገባ የግሩፑ ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ ጋዲሳ ግርማ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።
" ብዙ የኮንስትራክሽን ስራዎቹ ተገባደዋል። ፊንሺንግ ላይ እየሰራን ነው። አሁን ሁሉንም እቃዎች አስገብተን ጨርሰናል። በሁለት፣ ሦስት ወራት ወደ ስራ ይቀላቀላል ብለን ተስፋ እናደርጋለን " ሲሉ ነግረውናል።
ምን ያክል ሠራተኞች ለማሰማራት ታቅዷል ? ለሚለው ጥያቄ፣ ግሩፑ ጎንደር በኪራይ የሚሰራ ሆቴልና ሪዞርት ስላለው ያሉት ሠራተኞች እንደሚቀጥሉ፣ ተጨማሪ የሰው ኃይል ደግሞ እየታዬ እንደሚጨር አስረድተዋል።
ሆቴሉ ምን ያክል ክፍሎች አሉት ? ወጪውስ ምን ያክል ነው ? ለሚለው ጥያቄ፣ " ወጪዎቹ ገና አልተሰሩም፤ ገና የግንባታ ስራው ስላላለቀ። ወደ 84 አካባቢ ሩሞች አሉት " ሲሉ ገልጸዋል።
ጎንደር በኪራይ የሚሰራ ሆቴልና ሪዞርት እንዳላቸው የእነርሱ ግንባታ ሲጠናቀቅ በኪራይ ያለውን አገልግሎት ይዘው የመቀጠል አቅድ እንዳላቸው ገልጸው፣ ጎንደር ሆቴልና ሪዞርት 12ኛ መዳረሻ እንደሚሆን አስረድተዋል።
" ኮንስትራክሽን ላይ ቀናትን የሚወስኑ ብዙ ጉዳዮች ስላሉ ሆቴሉ በትክክል የሚመረቅበት ቀን ገና አልተወሰነም። እቅዳችን ከሁለት እስከ ሦስት ወራት ባለው ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ወደ ስራ ማስገባት ነው " በማለትም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
አማራ ክልል የጸጥታ ችግር ያለበት ከመሆኑ እንዲሁም ደግሞ፣ ከኮንስትራክሽን እቃዎች መወደድ ጋር በተያያዘ የገጠሟቸው ችግሮችን እንዲገልጹ ስንጠይቃቸው ደግሞ፣ " እቃ ጨምሯል። የመጣውን እንደ አመጣጡ ማኔጅ ማድረግ ነው እንጅ ቻሌንጆች አሉ። ቻሌንጅን አልፎ መስራት ነው የኛ እምነት " ብለዋል።
ከወራት በፊት ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ የነበራቸው አቶ ጋዲሳ ግርማ፣ ጎንደር ላይ በኪራይ እየተሰራ መሆኑና እየተገነባ ያለው ባለአራት ኮከብ ሆቴልና ሪዞርት መሆኑን ገልጸው ነበር።
" ዘመናዊ አርኪቴክቸራል እየተጠቀም ነው። ግንባታው ይበልጥ ባህላዊ እና አካባቢውን በሚመስል መልኩ ነው የተሰራው። ለምሳሌ ህንፃው ፋሲለደስ በተሰራበት መንገድ የተሰራ ነው። ከአካባቢው ጋር እንዲመሳሰል ታስቦበት ስለተሰራ ይበልጥ ይጨበጭብለታል " ነበር ያሉን።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 19 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia