#ጥናት
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

#ጥናት
በትግራይ የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያዎች ከፍተኛ የአገልግሎትና የጥበቃ ክፍተት እንዳለ ጥናት አመላከተ።
በትግራይ ክልል የሚገኙ የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያዎች በምግብ፣ በውሃና ንፅህና፣ በጤና፣ በመጠለያ እና በጥበቃ አገልግሎቶች ላይ ከፍተኛ ክፍተት እንዳለባቸው በቅርቡ ይፋ የሆነ ጥናት አመላክቷል።
ጥናቱ በ5 ዞኖችና በ21 ወረዳዎች የሚገኙ 78 የተፈናቃይ ጣቢያዎችን የሸፈነ ሲሆን፣ ውጤቱ ወደ 307 ሺህ የሚጠጉ ተፈናቃዮችን የሚመለከት መሆኑ ተገልጿል። ጥናቱ በዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) በበላይነት የተካሄደ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ የካምፕ አስተባባሪነትና አስተዳደር ክላስተር (CCCM) እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
በጥናቱ መሠረት 95 በመቶ የሚሆኑት ጣቢያዎች የምግብ ድጋፍ ቢያገኙም፣ ድጋፉ የተፈናቃዮችን ፍላጎት ለመሸፈን በቂ አለመሆኑ ተጠቁሟል። ተመሳሳይ ክፍተት በስነ-ምግብ፣ በጤና፣ በውሃና ንፅህና፣ በትምህርትና በመጠለያ አገልግሎቶችም ታይቷል።
ከ78ቱ ጣቢያዎች 45ቱ ምንም የጥበቃ አገልግሎት የሌላቸው ሲሆን፣ 36 ጣቢያዎች ደግሞ ምንም የመጠለያ ድጋፍ እንደማያገኙ ጥናቱ ያሳያል።
በውሃና ንፅህና ዘርፍም 4 ጣቢያዎች ብቻ በቂ አገልግሎት ሲኖራቸው፣ 27 ጣቢያዎች ምንም አገልግሎት የላቸውም፤ በ47 ጣቢያዎች ደግሞ አገልግሎቱ በቂ አለመሆኑ ተመልክቷል።
በተለይ የጣቢያ አስተዳደርና ማስተባበር ላይ ከፍተኛ ክፍተት መኖሩ ተጠቁሟል። ከተገመገሙት 78 ጣቢያዎች 37ቱ የተፈናቃዮችን ቁጥርና ፍላጎት መከታተል፣ ከሰብዓዊ ድርጅቶች ጋር ማስተባበር፣ መረጃ ማድረስና ቅሬታ መቀበል የሚችል የCCCM አካል የላቸውም።
ችግሩ በማዕከላዊ ዞን ይበልጥ የጎላ ሲሆን፣ በዞኑ የሚገኙ የተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያዎች ሁሉም የCCCM አገልግሎት እንደሌላቸው ጥናቱ ጠቁሟል። ዞኑ ከትግራይ አጠቃላይ ተፈናቃይ ህዝብ 19 በመቶ የሚያስተናግድ መሆኑም ተገልጿል።
ከጥበቃ አንፃርም የህጻናት ጥበቃ ስጋት በ64 ጣቢያዎች፣ የሴቶችና ሴት ልጆች ደህንነት ስጋት በ55 ጣቢያዎች እና የፆታዊ ጥቃት ስጋት በ46 ጣቢያዎች መኖሩ ተለይቷል። በተጨማሪም 39 ጣቢያዎች የአካል ጉዳተኞች ተደራሽነት ችግር፣ 14 ጣቢያዎች የመሬትና ንብረት ክርክር፣ 12 ጣቢያዎች ከአስተናጋጅ ማህበረሰብ ጋር ውጥረት እና 10 ጣቢያዎች የሰነድ እጦት እንዳለባቸው ተጠቁሟል።
በአጠቃላይ ከ78ቱ ጣቢያዎች 44ቱ መካከለኛ፣ 22ቱ ከፍተኛ እና 10ሩ ደግሞ ወሳኝ የስጋት ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ጥናቱ ደርሷል። 70 በመቶ የሚሆኑት ጣቢያዎች የአካባቢ ስጋት ሲያመለክቱ፣ 43 በመቶዎቹ ደግሞ እንደ ወቅታዊ ጎርፍ ያሉ አደጋዎችን እንደሚጋፈጡ ተገልጿል።
ጥናቱ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ ፈንድ (EHF) እና በአውሮፓ ህብረት የገንዘብ ድጋፍ መካሄዱ ታውቋል።
ስለጥናቱ ሂደትና ውጤቶቹ ላይ ግንዛቤ እንዳለው የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia