#BRICS+
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

#BRICS+
የ2026 የብሪክስ ጉባኤ በህንድ ኒው ዴልሂ ዛሬ ተጀምሯል።
የሁለት ቀን ጉባኤው በህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ሲሆን፣ የብሪክስ አባል ሀገራት መሪዎችና ከፍተኛ ባለሥልጣናት ተሳትፈዋል።
በጉባኤው ላይ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተገኝተዋል።
ጉባኤው የአባል ሀገራትን የኢኮኖሚ ትብብር ማጠናከር፣ የዓለም ደቡብ ሀገራትን ድምፅ ማሳደግ፣ የንግድና የፋይናንስ ትብብርን ማስፋፋት እና በዓለም ላይ እየተፈጠሩ ላሉ የጂኦፖለቲካ ችግሮች የጋራ አቋም ማስቀመጥ ላይ ያተኩራል።
በተለይም በዩክሬንና በመካከለኛው ምሥራቅ የቀጠሉ ጦርነቶች፣ የኃይል አቅርቦትና የዓለም ንግድ መስተጓጎሎች፣ የንግድ ቀረጦች እና የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት በዋና ከውይይት አጀንዳዎች መካከል ናቸው።
በጉባኤው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፣ የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ፣ የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የኢራን ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን ጨምሮ በርካታ የአባል ሀገራት መሪዎች ተገኝተዋል።
የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ፣ የዓለም ደቡብ ሀገራት በዓለም አቀፍ ቀውሶች በተለይ ተጎጂ ሆነው ሳለ በውሳኔ አሰጣጥ ሂደት በቂ ድምፅ እንደሌላቸው ገልጸው፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት እንዲሻሻሉ ጠይቀዋል። በተለይም የተመድ የጸጥታ ምክር ቤት ለውጥ ከእንግዲህ ሊዘገይ እንደማይገባ አስገንዝበዋል።
ከጉባኤው በፊት የብሪክስ አባላት የጋራ መግለጫ ላይ መስማማታቸውም ተገልጿል። መግለጫው የትኛውንም ሀገር በስም ሳይጠቅስ በአንድ ወገን የሚደረግ ጦርነትን የሚያወግዝ አቋም እንደሚያካትት የሮይተርስ ምንጮች ገልጸዋል።
ብሪክስ በአሁኑ ወቅት ከ40 በመቶ በላይ የዓለምን ሕዝብ የሚወክል እና ወደ አንድ አራተኛ የሚጠጋ የዓለም ኢኮኖሚ ድርሻ ያለው ቡድን ሆኗል።
በመሆኑም የ2026 የብሪክስ ጉባኤ የኢኮኖሚ ትብብርን ከማጠናከር ባለፈ፣ በተለዋዋጭ የዓለም ሥርዓት ውስጥ የዓለም ደቡብ ሀገራት የበለጠ ድምፅና ተጽዕኖ እንዲኖራቸው የሚደረገውን ጥረት ለማሳየት አስፈላጊ መድረክ ሆኗል።
መስከረም 2 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia