⚠️ #CONTENT_WARNING - ይህ ቪድዮ የሚረብሽ እና ስሜትን የሚነካ በመሆኑ በጥንቃቄ ይመልከቱ።
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·
⚠️ #CONTENT_WARNING - ይህ ቪድዮ የሚረብሽ እና ስሜትን የሚነካ በመሆኑ በጥንቃቄ ይመልከቱ።
በህንድ ሀገር በአንድ የግል ትምህርት ቤት የ6 ዓመት ህፃን በመምህሩ በጥፊ ከተመታ በኋላ ህይወቱ አልፏል።
ክስተቱ በትምህርት ቤቱ የክፍል ውስጥ የደኅንነት ካሜራ ተቀርጾ ወጥቷል።
መምህርቷ ህጻኑን " የቤት ስራ አልሰራህም " በማለት በጥፊ እንደመታችው ተገልጿል።
በደህንነት ካሜራው ላይ እንደታየው ህፃኑ በመምህሩ በጥፊ ከመመታቱ በፊት ፣ በከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ ሆኖ ሲንቀጠቀጥና መምህሩን ሲለምን ነበር። በኋላ በጥፊ ከተመታ በኋላ ተዝለፍልፎ መምህርቷ ላይ ወድቋል።
በሰዓቱ ርብርብ ተደርጎ ወደ ጤና ተቋም ቢወሰድም ህይወቱ ግን ሊተርፍ አልቻለም።
የህጻኑ ሞት ትክክለኛ ምክንያትና በመምህሩ ድርጊት እና በህፃኑ ሞት መካከል ያለው ቀጥተኛ ግንኙነት በምርመራ እየተጣራ መኑን የህንድ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ክስተቱ በትምህርት ቤቶች ህፃናትን ከአካላዊ ቅጣት መጠበቅና የተማሪዎችን ደኅንነት ማረጋገጥ ላይ ጥያቄ ያስነሳና ዓለም አቀፋዊ መነጋገሪያ የሆነ ነው።
ቪድዮ ፦ አልጀዚራ
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia