ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

" የዝንጀሮ መንጋው ጥቃት ብሶብናል " - የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች
👉 " 10 የመንጋ መሪ ዝንጀሮዎችን ቀንሰናል፤ ችግሩን በመሰረታዊነት ለመፍታት የሆቴሎች ተረፈ ምርት አወጋገድ ላይ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል " - ነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ
ከአንድ ወር በፊት የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ባቀረቡት ቅሬታ ከነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ የሚወጣ የዝንጀሮ መንጋ ልዩ ልዩ ጉዳቶችን ማድረሱን ተከትሎ ነዋሪዎች ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት በመውሰዳቸውና ፍርድ ቤቱም " የመንጋ መሪዎችን ቀንሱ " የሚል ትዕዛዝ መስጠቱን እንዲሁም ፓርኩ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን መግለፁን መዘገባችን አይዘነጋም።
ሆኖም ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉ የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ፓርኩ የተባለውን ያክል እርምጃ አለመውሰዱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
" የዝንጀሮ መንጋው ብሶትና በቀል ያለበት ይመስል አሁን ላይ ጥቃቱና ውድመቱ ይበልጥ በርትቶብናል " ሲሉ ድጋሚ ቅሬታቸውን ገልጠዋል።
በተጨማሪም ጉዳዩን በፍርድ ቤት ይከታተሉ የነበሩ አንድ ነዋሪ እንደገለጹት፤ ፓርኩ ለፍርድ ቤት " የመንጋ መሪዎችን ቀንሻለሁ " በማለት ያቀረበው የስድስት ዝንጀሮዎች ፎቶ የሶስት ብቻ መሆኑን ፍርድ ቤቱ አረጋግጦ በድጋሚ ለፓርኩ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን አንስተዋል።
በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሰጡት የነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ የማህበረሰብ አገልግሎት አስተባባሪ ፤ ፓርኩ አሰራሩን ተከትሎ 10 የመንጋ መሪ ዝንጀሮዎችን መቀነሱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
አስተባባሪው አክለውም፤ ችግሩን በዘላቂነትና በመሰረታዊነት ለመፍታት በከተማዋ የሚገኙ ሆቴሎች የምግብ ተረፈ-ምርቶችን በሚያስወግዱበት ወቅት አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia