#USA
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

#USA
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአረብና የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ አማካሪ ማሳድ ቡሎስ፣ " አሜሪካ ከኤርትራ ጋር በመሆን በአፍሪካ ቀንድ ያለች አንድ አገር ላይ ምሥጢራዊ ድርድር ወይም ስምምነት ላይ ለመድረስ እየሞከረች ነው " የሚሉ ወሬዎችን ፍጹም ሐሰት ናቸው አሉ።
ቡሎስ፣ አሜሪካ ከኤርትራ ጋር በማንኛውም የቀጣናው አገር ላይ ሴራ እየሠራች አይደለችም፤ እንዲህ ዓይነት ስምምነትም ሆነ ድርድር ፈጽሞ የለም ብለዋል።
ማሳድ ቡሎስ የተጠቀሰው አገር የትኛው እንደሆነ በስም ባይገልጹም፣ በቅርብ ጊዜ በቀጠናው እየተነሱ ያሉ ውይይቶች ከኢትዮጵያ ጋር ተያይዘው እየተተረጎሙ ናቸው።
አማካሪው እንዳሉት፣ የአሜሪካ ዋነኛ ዓላማ በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን ማጠናከር እንጂ አገራትን ለማጋጨት ወይም ተቀናቃኝ ጎራዎችን ለመፍጠር አይደለም።
መሠረት የሌላቸው ወሬዎች የሰላም ጥረቶችን እንደሚያደናቅፉ ጠቁመዋል።
ቡሎስ በቅርቡ በካይሮ ከግብፅ፣ ከኤርትራ እና ከሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ውይይት አድርገው የነበረ ሲሆን በወቅቱ ውይይቱ ፀረ ኢትዮጵያ ነበር የሚሉ ዘገባዎች ቢወጡም፣ ቡሎስ እነዚህን "ሐሰተኛና አሳሳች" ብለዋቸዋል።
እንደ ቡሎስ ገለጻ አሜሪካ ከኢትዮጵያ፣ ከኤርትራ፣ ከግብፅ እና ከሌሎች የአፍሪካ ቀንድ አገራት ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ መሥራቷን ትቀጥላለች፤ ከአንድ አገር ጋር የሚደረግ ግንኙነትም ከሌላ አገር ጋር ጠላትነት ማለት እንዳልሆነ አስረድተዋል።
መረጃው የቢቢሲ ነው።
ሃምሌ 29 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia