#USA #Immigration
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

#USA #Immigration
በአሜሪካ ጥገኝነት ጠያቂዎች ያለ ቃለ-መጠይቅ ወደ ፍርድ ቤት የሚላኩበት መመሪያ ጸደቀ።
የትራምፕ አስተዳደር በሀገሪቱ ጥገኝነት የጠየቁ ስደተኞችን የሚመለከት አዲስ መመሪያ አውጥቷል።
ይህን ተከትሎ በርካታ ጥገኝነት ጠያቂዎች ጉዳያቸው ሳይሰማ ቀጥታ ሊባረሩ የሚችሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል።
አዲሱ አሰራር ከ1.4 ሚሊዮን በላይ የተከማቹ የጥገኝነት ማመልከቻዎችን ለማቃለል የታሰበ ነው ተብሏል።
ቀደም ሲል የነበረው አሰራር አመልካቾች መጀመሪያ ጉዳያቸውን ለኢሚግሬሽን ኦፊሰር አቅርበው ጥያቄያቸው ውድቅ ከተደረገ ብቻ ወደ ፍርድ ቤት እንዲመሩ የሚያደርግ ነበር።
በአዲሱ መመሪያ በርካታ የጥገኝነት አመልካቾች ከኢሚግሬሽን ኦፊሰሮች ጋር የሚደረገውን የመጀመሪያ ደረጃ ቃለ-መጠይቅ ሳያደርጉ ጉዳያቸው በቀጥታ ወደ ፍርድ ቤት ሊመራ ይችላል።
444,724 ያህል መዝገቦችን ይነካል የተባለው ይህ ውሳኔ የሕግ ባለሙያዎችና የኢሚግሬሽን ተከራካሪዎች አሰራሩ የስደተኞችን የመሰማትና የፍትህ የማግኘት መብት የሚጎዳና ውሳኔዎችን በማፋጠን ሰዎችን በፍጥነት ለማባረር ያለመ ነው በማለት ተችተውታል።
በሌላ በኩል ፥ የአሜሪካ መንግሥት በሀገሪቱ በሚማሩ የውጭ ሀገር ተማሪዎች ላይ እስከ 100,000 ዶላር የሚደርስ አዲስ ክፍያ ለመጣል ማቀዱ ተሰምቷል።
የታቀደው እርምጃ በተለይ ትምህርታቸውን አጠናቀው በአሜሪካ ለመቆየት ለሚፈልጉ ዓለም አቀፍ ተማሪዎች ፈተና ሊሆን እንደሚችል ተገልጿል።
መንግሥት እርምጃው የቪዛ አጠቃቀምን ለማጥበቅና የሀገር ውስጥ የሥራ ገበያን ለመጠበቅ ያለመ መሆኑን ሲገልጽ፣ ተቃዋሚዎች ግን የውጭ ተማሪዎች ለአሜሪካ የትምህርትና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያላቸውን አስተዋፅኦ ሊጎዳ ይችላል በማለት ስጋታቸውን ገልጸዋል።
የትራምፕ አስተዳደር ከስደተኞች ጋር በተያያዝ እጅግ ጠንካራ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑ ተደጋግሞ መገለጹ ይታወሳል።
ሃምሌ 24 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia