ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

#MadridDerby

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
#MadridDerby
#MadridDerby

ተጠባቂው የማድሪድ ደርቢ በሪያል ማድሪድ እና አትሌቲኮ ማድሪድ መካከል በሪያድ ኤር ሜትሮፖሊታኖ ስታዲየም ላይ ይደረጋል።

ሪያል ማድሪድ በአስራ አምስት ነጥቦች ሁለተኛ ደረጃ ላይ ሆኖ የደርቢ ጨዋታውን ያደርጋል።

ባለሜዳው አትሌቲኮ ማድሪድ በበኩሉ በአስራ ሶስት ነጥቦች አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

የትኞቹ ተጨዋቾች አይገኙም ?

ሎስ ብላንኮዎቹ የጉዳት ስጋት የሌለባቸው ሲሆን ሁሉም ተጨዋቾች ለደርቢው ዝግጁ ናቸዉ።

በአትሌቲኮ ማድሪድ በኩል ፓብሎ ባርዮስ ሪቫስ ከጨዋታው ውጪ እንደሆነ ተገልጿል።

ጨዋታውን ማን ይመራዋል ?

ጨዋታውን ከማድሪድ ከተማ የተገኙት ዳኛ ኦርቲዝ አርያስ በመሐል ዳኝነት እንዲመሩ ተመርጠዋል።

ዳኛው የማድሪድ ደርቢን የመሩ የመጀመሪያው የማድሪድ ዳኛ በመሆን አዲስ ታሪክ ይፅፋሉ።

ቁጥራዊ መረጃዎች ?

ኪሊያን ምባፔ በስድስት ጨዋታዎች ሰባት ጎሎችን በማስቆጠር የክለቡ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ነው።

አሌክስ ቤና በአራት ግቦች የአትሌቲኮ ማድሪድ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪው ተጨዋች ሆኗል።

በሊጉ የጎል ልዩነት ደረጃ ሪያል ማድሪድ በ 11 እንዲሁም አትሌቲኮ ማድሪድ በ 8 ንፁህ ግብ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች