ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ፒኤስጂ ወይስ ኦሎምፒክ ማርሴይ ?

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ፒኤስጂ ወይስ ኦሎምፒክ ማርሴይ ?
ፒኤስጂ ወይስ ኦሎምፒክ ማርሴይ ?

በፈረንሳይ ሊግ ፒኤስጂ ከኦሎምፒክ ማርሴይ ጋር የ ሌ ክላሲኮ ደርቢ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ደካማ የውድድር አመት ጅማሮ ያደረገው ፒኤስጂ ከሊጉ መሪ ሞናኮ በስምንት ነጥቦች ርቆ ይገኛል።

የአሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬው ቡድን ይህን የነጥብ ልዩነት ለማጥበብ በማለም ወደ ሜዳ ይገባል።

ፒኤስጂ ከመጀመሪያው አራት ጨዋታዎች ሁለቱን አቻ ሲወጣ በአንዱ ተሸንፎ በአንዱ አቻ ተለያይቷል።

በዛሬው ጨዋታ ፒኤስጂ የአሽራፍ ሀኪሚ እና ሉካስ ሄርናንዴዝን ግልጋሎት የማያገኝ ይሆናል።

ማርሴይ በበኩሉ ከመጀመሪያ አራት ጨዋታዎች ሶስቱን በሽንፈት ያጠናቀቀ ሲሆን ቀሪውን አሸንፏል።

ሁለቱ ቡድኖች ካሉበት የውጤት ማጣት ለመውጣት ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የእርስ በርስ ግንኙነታቸው ምን ይመስላል ?

ሁለቱ ክለቦች በታሪክ አጋጣሚ 112 ጊዜ ሲገናኙ ፒኤስጂ 53 ጊዜ ያሸነፈ ሲሆን ማርሴይ በ 35 ረቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች