ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ሀል ሲቲ ተጨዋቹ የዘረኝነት ጥቃት ሰለባ ሆነ !

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ሀል ሲቲ ተጨዋቹ የዘረኝነት ጥቃት ሰለባ ሆነ !
ሀል ሲቲ ተጨዋቹ የዘረኝነት ጥቃት ሰለባ ሆነ !

የፕሪሚየር ሊጉ ክለብ ሀል ሲቲ አዲሱ ፈራሚው ሮቢንዮ ቫዝ የዘረኝነት ጥቃት ሰለባ ሆኗል።

ተጨዋቹ ለሀል ሲቲ ከፈረመ በኋላ በማህበራዊ ሚዲያው ከፍተኛ የዘረኝነት ጥቃት ደርሶበታል።

በዚህም ምክንያት ሀል ሲቲ ተጫዋቹን ማስፈረሙን ይፋ ያደረገበትን ፖስት ለማጥፋት ተገዷል።

በተጨማሪም ሀል ሲቲ የሌሎች ፖስቶችን የአስተያየት መስጫ ሳጥኖች ለማጥፋት ተገዷል።

ሀል ሲቲ ተጨዋቹ ላይ የደረሰውን የዘረኝነት ጥቃት ባወጣው ይፋዊ መግለጫ አውግዟል።

ክለቡ ከፖሊስ ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን በማሳወቅ ሊጉን እና ዘረኝነትን የሚቃወሙ ተቋማት ማነጋገሩን ገልጿል።

ሀል ሲቲ ፈረንሳዊውን የ 19ዓመት አጥቂ ቫዝ ከሮማ በ 32 ሚልዮን ዩሮ ነበር ያስፈረሙት።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች