ማንችስተር ዩናይትድ ባሌባን ለምን ፈለገው ?

ማንችስተር ዩናይትድ ባሌባን ለምን ፈለገው ?
ማንችስተር ዩናይትድ ባለፈው ክረምት ካርሎስ ባሌባን ለማስፈረም ከፍተኛ ጥረት አድርጎ ነበር።
ከዛን ጊዜ በኋላ ካሜሮናዊው አማካይ ካሮሎስ ባሌባ በብራይተን አስቸጋሪ የውድድር ዘመን አሳልፏል።
ይሁን እንጂ ባሌባ በሊጉ የነበሩት ድንቅ ሁለት አመታት እና ያሉት ቁጥሮች አሁንም ማንችስተር ዩናይትድ እንዲመለከተው አድርጓል።
ማንችስተር ዩናይትዶች ባሌባ በአፍሪካ ዋንጫው ከብሪያን ምቤሞ ጋር ሲጫወት ሲመለከቱት እንደነበር ተገልጿል።
ተጨዋቹ በአፍሪካ ዋንጫው ባደረጋቸው አምስት ጨዋታዎች ያሳየው እንቅስቃሴ ማንችስተር ዩናይትድን አስደንቋል።
ማንችስተር ዩናይትድ ካርሎስ ባሌባ ያለው ቁጥር ቡድኑ ከሚፈልገው ጋር የሚጣጣም ነው የሚል እምነት እንዳላቸው ተነግሯል።
ክለቡ ባሌባ ሜዳውን የማካለል ፣ ኳስ መልሶ የማግኘት እና ትክክለኛ ኳስ የማቀበል ክህሎቱን ያደንቃል።
በተጨማሪም ግራ እግር እንደመሆኑ አስፈላጊ ሲሆን የግራ መስመር ቦታውን ክፍተት ይሸፍናል የሚል እምነት አላቸው።
ካርሎስ ባሌባ ባለፈው አመት በአስራ አምስት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ ተቀይሮ ወጥቶ ነበር።
ማንችስተር ዩናይትድ ባለፈው ክረምት እሱን ለማስፈረም ከፍተኛ ጥረት ማድረጉ እና ጉዳት በአቋሙ ላይ ተፅዕኖ እንዳሳደረ ተገልጿል።
በብራይተን ተጨዋቹ በራስ መተማመኑን መልሶ እንዲያገኝ እርዳታ ሲደረግለት እንደነበር ተነግሯል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe