ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ በቡድኑ በጣም ደስተኞች ነን ” ዣቢ አሎንሶ

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ በቡድኑ በጣም ደስተኞች ነን ” ዣቢ አሎንሶ
“ በቡድኑ በጣም ደስተኞች ነን ” ዣቢ አሎንሶ

የቼልሲው አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ ከፕሪሚየር ሊጉ መክፈቻ ጨዋታ በፊት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ዣቢ አሎንሶ ስለ ኢንዞ ፈርናንዴዝ ተጠይቀው “ እሱ የቼልሲ ተጨዋች ነው እሱ በትልቅ ደረጃ ያለ ተጨዋች ነው "ብለዋል።

“ እሱ ስላለን ደስተኞች ነን ሰኞ ላለብን ጨዋታ እየተዘጋጀ ነው “ ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል።

“ በቡድኑ ደስተኞች ነን “ ያሉት ዣቢ አሎንሶ ብዙ ትክክለኛ ምርጫዎች አድርገናል አሁን በጥሩ ሁኔታ ላይ ነን "ብለዋል።

ስለ ፉልሀም አሰልጣኝ አርቤሎኣ የተጠየቁት ዣቢ አሎንሶ " ጥሩ ግንኙነት አለን ነገርግን ሜዳ ላይ ስንገባ ጓደኝነት የለም ለዘጠና ደቂቃ እንፋለማለን "ብለዋል።

ቼልሲ የፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታውን ሰኞ ምሽት 4:00 ሰዓት ከፉልሀም ጋር ያደርጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች