ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ ባሎን ዶር ለማሸነፍ በሚዲያ አልለምንም ” ላሚን ያማል

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ ባሎን ዶር ለማሸነፍ በሚዲያ አልለምንም ” ላሚን ያማል
“ ባሎን ዶር ለማሸነፍ በሚዲያ አልለምንም ” ላሚን ያማል

“ ከሁሉም የተሻለ አመት ያሳለፍኩት እኔ ነኝ ”

የባርሴሎናው ኮከብ ላሚን ያማል ባሎን ዶር ሽልማት በልመና መውሰድ አልፈልግም ሲል ተናግሯል።

ስለ ባሎን ዶር ጥያቄ የተነሳለት ያማል “ ለማሸነፍ በሚዲያ ልመና አልወጣም “ ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።

አክሎም “ የማሸንፍ ከሆነ አመስጋኝ እሆናለሁ በተለይ በክለብ እና በሀገር የነበሩኝን የቡድን አጋሮች “ ሲል ገልጿል።

ዴምቤሌ ከምርጥ ሶስት ውስጥ እንዳላካተተው የተነገረው ያማል “ እሱ የምባፔ ጓደኛ ነው " ሲል መልሷል።

“ ባሳለፍኩት የውድድር አመት እኮራለሁ ” ያለው ላሚን ያማል “ የአለም ሻምፒዮን ነን ሊጉንም ዳግም አሸንፈናል "ብሏል።

“ ካሉት ከሁሉም ተወዳዳሪ ተጨዋቾች እኔ ምርጥ የውድድር አመት አሳልፊያለሁ ጠንክሬም ሰርቻለሁ “ ላሚን ያማል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች