ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

አርሰናል እንደ ቪንሰስ አይነት ተጨዋች ለምን ፈለገ ?

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
አርሰናል እንደ ቪንሰስ አይነት ተጨዋች ለምን ፈለገ ?
አርሰናል እንደ ቪንሰስ አይነት ተጨዋች ለምን ፈለገ ?

የወቅቱ የፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ አርሰናል ቪንሰስ ጁኒየርን ለማስፈረም ማሰቡ መዘገቡ አይዘነጋም።

መድፈኞቹ የግራ የፊት መስመራቸውን ለማጠናከር ቪንሰስ ጁኒየርን ለመውሰድ አልመዋል።

ባለፈው አመት የአርሰናል የግራ መስመር ቦታ ያን ያህል ጠንካራ አልነበረም ማርቲኔሊ እና ትሮሳርድ በጋራ ሰባት ጎሎች ነበር ያስቆጠሩት።

ስለሆነም አርሰናል አብዛኛውን የማጥቃት እንቅስቃሴ በቀኝ በኩል ያደረገ ሲሆን ይህንንም ተጋጣሚዎች በቀላል እንዲገምቱት አድርጎ ነበር።

አሁን ላይ ክለቡ ቦታውን ለማጠናከር ቅድሚያ የሰጠ ሲሆን ሊጉን ዳግም ለማሳካት ቪንሰስ ጁኒየር ሁነኛ መፍትሄ ተደርጎ ታይቷል።

ቪንሰስ ጁኒየር ጥሩ ኳስ አታሎ የማለፍ ፤ ኳስ የመቆጣጠር እና አክርሮ የመምታት ክህሎት ይዟል።

ባለፈው የውድድር ዘመን በላሊጋው ከቪንሰስ ጁኒየር በላይ ብዙ ኳስ አታሎ ለማለፍ የሞከሩ ተጨዋች ሶስት ናቸው።

በአለም ላይ እንደ ቪንሰስ ጎል የማስቆጠር እና አመቻችቶ የማቀበል ስጋት መፍጠር የሚችሉ የክንፍ ተሰላፊዎች ጥቂት እንደሆኑ ቁጥሮች ያሳያሉ።

ቪንሰስ በጠባብ ክፍተት ግብ ማስቆጠር የሚችል እና ጥሩ የማግባት እድል ላለው ተጨዋች ኳስ ለማቀበል የማይቸገር ተጨዋች ነው።

ሚኬል አርቴታ ቪንሰስን እንዲወዱ ያደረጓቸው ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩም አርሰናል በእሱ የሚፈቱለት ታክቲካል ችግሮችም ይኖራሉ።

አርሰናል ከሚያጠቃ ቡድን ጋር ሲጫወት ቪንሰስ በፈጣን መልሶ ማጥቃት የሚፈጥረውን ስጋት በመፍራት ተጋጣሚዎች ሁሉንም ተጨዋቾች ወደፊት እንዳያወጡ ያደርጋቸዋል።

ከመጨረሻ ተከላካይ ስር የማይጠፋው ቪንሰስ ኳስ ሲጣልለት ተከላካዮችን በፍጥነቱ በማለፍ ጨዋታውን በሚፈለገው መልኩ መቀየር ይችላል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች