ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ የዳኞች ማህበር እንኳን ደስ አላችሁ ” ጆዜ ሞሪንሆ

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ የዳኞች ማህበር እንኳን ደስ አላችሁ ” ጆዜ ሞሪንሆ
“ የዳኞች ማህበር እንኳን ደስ አላችሁ ” ጆዜ ሞሪንሆ

የሪያል ማድሪዱ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ከደርቢው ሽንፈት በኋላ የጨዋታው ዳኞች ላይ ጠንካራ ትችት ሰንዝረዋል።

ጆዜ ሞሪንሆ ከጨዋታው በኋላ በሰጡት ቃል “ ይህንን ዳኛ የመደባችሁ የዳኞች ኮሚቴ እንኳን ደስ አላችሁ "ሲሉ ገልጸዋል።

የዳኛው ማንነት የሚገለጸው ከጨዋታው 24ሰዓት በፊት መሆኑን ያስረዱት ሞሪንሆ “ ከሳምንት በፊት መታወቁ እንግዳ ነገር ነው ” ብለዋል።

“ ዳኛው ጨዋታውን መዳኘት አይገባውም “ ያሉት አሰልጣኙ “ እሱ አንድም አለም አቀፍ ጨዋታ አልዳኘም ለምን ካላችሁ አቅም የለውም “ብለዋል።

ስለ ሊጉ ዋንጫ ፉክክር የተጠየቁት ጆዜ ሞሪንሆ “ ብቻችንን የምትተዉን ከሆነ ጊዜ አለ ገና "ሲሉ መልሰዋል።

አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ አክለውም “ ዳኞች እባካችሁ እንድንፎካከር ፍቀዱልን ” ሲሉ ጠይቀዋል።

ሪያል ማድሪድን ያስቆጣው አንዱ ጥፋት የተሰራበት ቫልቬርዴ ለሶስት ሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች