ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ ደጋፊዎች ፊት ደስታዬን የገለፅኩት ቤተሰቤን ስለሰደቡ ነው ” ሊያም ሮሴንየር

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ ደጋፊዎች ፊት ደስታዬን የገለፅኩት ቤተሰቤን ስለሰደቡ ነው ” ሊያም ሮሴንየር
“ ደጋፊዎች ፊት ደስታዬን የገለፅኩት ቤተሰቤን ስለሰደቡ ነው ” ሊያም ሮሴንየር

ትናንት በተደረገ 5ኛ ሳምንት የፈረንሳይ ሊግ መርሐ ግብር ፓሪስ ስትራስቡርግን 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

በጨዋታው በአሰልጣኝ ሊያም ሮሴንየር እና የስትራስቡርግ ደጋፊዎች አለመግባባት ውስጥ ገብተው ነበር።

በጨዋታው ወቅት የስትራስቡርግ ደጋፊዎች አሰልጣኝ ሊያም ሮሴንየር ላይ የተለያዩ ስድቦችን ሲሰነዝሩ ተሰምተዋል።

የፓሪስ አሰልጣኝ ሊያም ሮሴንየር በበኩላቸው ከድሉ በኋላ የቀድሞ ክለባቸው ስትራስቡርግ ደጋፊዎች ፊት ሄደው ደስታቸውን ገልጸዋል።

ከድሉ በኋላ ለምን ያን እንዳደረጉ የተጠየቁት ሮሴንየር “ የተወሰኑ ደጋፊዎች የቤተሰቤን ክብር አሳጥተዋል ” ብለዋል።

“ ስኬቴን ለማይፈልጉ መልዕክት ማስተላለፍ ፈልጌ ነበር ፤ ስትራስቡርግን ምን ያህል እንደምወደው ሁሉም ያውቃል “ ሲሉ ተናግረዋል።

አሰልጣኙ ፓሪስን እየመሩ በዚህ አመት ያልተሸነፉ ሲሆን በ 11 ነጥቦች ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች