320 ነጥብ ያመጡት ቄስ ሰይፉ ተስፋይ !
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

320 ነጥብ ያመጡት ቄስ ሰይፉ ተስፋይ !
" ትምህርት ፍላጎትና ተነሳሽነት ካለ ዕድሜ አይገድበውም " የሚለውን እውነታ በተግባር ያሳዩት ቄስ ሰይፉ ተስፋይ፣ በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና 320 ነጥብ በማምጣት ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት ከሚጠባበቁ ተፈታኞች መካከል ተጠቃሽ ሆነዋል።
ቄስ ሰይፉ ተስፋይ በትግራይ ክልል፣ ደቡባዊ ዞን፣ ሰለዋ ወረዳ፣ ደጀን ቀበሌ፣ ግራዛፎ መንደር ነዋሪ ናቸው።
የ66 ዕድሜ ባለፀጋው ቄስ ሰይፉ፣ በሰለዋ ከተማ በሚገኘው የአንበሳ ባንክ የጥበቃ ሠራተኛ በመሆን እየሰሩ ነው። ከሥራቸው ጎን ለጎን ግን ትምህርታቸውን በመቀጠል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ለመፈተን ችለዋል።
በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በትግራይ ክልል ፈተናቸውን ከወሰዱ 29 ሺህ ተፈታኞች መካከል ቄስ ሰይፉም አንዱ ሲሆኑ፣ 320 ነጥብ በማምጣት የማለፊያ ውጤት ካመጡ 3,146 ተፈታኞች መካከል አንዱ ናቸው።
የቄስ ሰይፉ ውጤት በማህበራዊ ሚዲያ ትኩረት ያገኘ ሲሆን የሚሰሩበት ባንክም በተሳካላቸው ውጤት በመደሰት ሽልማት አበርክቶላቸዋል።
የቄስ ሰይፉ ታሪክ ትምህርት ለመማር ዕድሜ፣ ሥራ ወይም ሌላ ሁኔታ እንቅፋት እንዳልሆነ፣ ፍላጎትና ተነሳሽነት ካለ ሰው የፈለገውን ግብ ለማሳካት እንደሚችል ያሳያል።
ቄስ ሰይፉ ባለትዳርና የ6 ልጆች አባት ናቸው።
ነሐሴ 23 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia