#AddisAbaba
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

#AddisAbaba
ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ላልተወሰነ ጊዜ ተከለከለ።
ከዛሬ ከመስከረም 15 ቀን 2019 ጀምሮ ባለሁለት እግር ሞተር ብስክሌት በአዲስ አበባ ማሽከርከር እንደተከለከለ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አሳውቋል።
" አንዳንድ ወንጀል ፈጻሚዎች ሞተር ብስክሌትን በመጠቀም የቅሚያ እና የስርቆት ወንጀል ሲፈጽሙ ተይዘው ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል " ብሏል።
" ወንጀል ፈጻሚዎች ከቦታ ቦታ ለመዘዋወር እና የተሰረቁ እቃዎችን ለማጓጓዝ ሞተር ብስክሌትን በብዛት ይጠቀማሉ " ሲል ገልጿል።
ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች የትራፊክ ደንቡን እንደማያከብሩ በተለይ ፦
- ቀይ መብራትን መጣስ፣
- ሌሎች ተሽከርካሪዎችን በመግጨት ማምለጥ፣
- ሄልሜት ሳያደርጉ ማሽከርከር፣
- የተፋፋቀ እና ለእይታ አስቸጋሪ የሆኑ የሠሌዳ ቁጥሮችን መጠቀም በአሽከርካሪዎቹ በስፋት የሚስተዋሉ የደንብ ጥሰቶች መሆናቸውን ፖሊስ አመልክቷል።
ወንጀልን ለመከላከል እና በሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች የሚፈጸምን የደንብ ጥሰት ለመቆጣጠር ከዛሬ ከመስከረም 15 ቀን 2019 ዓ/ም ጀምሮ ከኮድ 4 እና ከፖሊስ ሞተር ብስክሌት ውጭ በአዲስ አበባ ከተማ ባለ ሁለት እግር ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር መከልከሉን ፖሊስ አሳቋል።
የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች እና ባለ ንብረቶች የተባለው እንዲያከብሩ ፤ ነገር ግን ይህንን ማሳሳቢያ በሚተላለፉ ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ማስጠንቀቂያ ተላልፏል።
#AddisAbabaPolice
መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia