ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳት እና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በመስቀል ደመራ በዓል ወቅት ህብረተሰቡ ከአደጋ እንዲጠነቀቅ አሳሰበ።

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳት እና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በመስቀል ደመራ በዓል ወቅት ህብረተሰቡ ከአደጋ እንዲጠነቀቅ አሳሰበ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳት እና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በመስቀል ደመራ በዓል ወቅት ህብረተሰቡ ከአደጋ እንዲጠነቀቅ አሳሰበ።

በየመስቀል ደመራ በዓል ወቅት፥ ህብረተሰቡ ከእሳት እና ኤሌክትሪክ ፍጆታ መጨመር፣ ከመዝናናት እንቅስቃሴ አንፃር በጥንቃቄ ጉድለት ሊደርሱ ለሚችሉ አደጋዎችን ቀድሞ ትኩረት በመስጠት ጥንቃቄ እንዲደረግ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አሳስቧል፡፡

ከኮሚሽኑ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ዘርፍ አቶ ሰሎሞን መኮንን፣ ለመስቀል ደመራ የሚሆነው ችቦ እርጥብ ሆኖ አልነድ ሲል በፈሳሽ ነዳጅ በማራስ ከማቀጣጠል መቆጠብ አንዱ የጥናቃቄ መንገድ መሆኑን አስገንዝበዋል።

አቶ ሰለሞን አክለው ባስተላለፉት መልዕክት ፦

- ችቦ በቤት ውስጥ ሲለኮስነ በቤት ወስጥ የሚገኙ ምንጣፎች እና መጋረጃዎች እንዳይቀጣጠሉ መጠንቀቅ፣

- ዘመናዊ ችቦ ወይም ርችት ሲለኮስ የአጠቃቀም ጥንቃቄ ማድረግ፣

- ርችቱ ተወርውሮ ሲሄድ በአካባቢው በሚገኙ በሳር ክምር፣ የሳር ክዳን ባላቸው ጎጆ ቤቶች፣ ነዳጅ ማደያ ዴፖዎችና ማደያ ጣቢያ ላይ እንዳያርፍ የጥንቃቄ መመሪያዎችን ተግባራዊ ማድረግ፣

- የመስቀል ደመራ የሚደመርበት ስፍራ ከነዳጅ ማደያ፣ ከኤሌክትሪክና ስልክ ምሰሶዎች እና መስመሮች የራቀ መሆኑን ማረጋገጥ፣

- ደመራ ተለኩሶ ተቀጣጥሎ ካለቀ በኋላ በውሃ ማጥፋት፣

- በምግብ ማብሰያ አካባቢ የኤሌክትሪክ ምድጃዎች፣ የቡታ ጋዝ፣ የጧፍ እና ከሰል ምድጃዎችን በአግባቡ እና በጥንቄ መጠቀም፣

- ሻማ እና ጧፍ በሚጠቀሙበት ወቅት ከተቀጣጣይ ነገር ማራቅ፣

- ጠጥቶ አለመሽከርከር፣ ለመዝናናት ገደብ መስጠት እንደሚገባ አሳስቧል።

እነዚህ ሁሉ ጥንቃቄዎች ተደርገው በአጋጣሚና ባልታወቀ ምክንያት በቤትም ሆነ በአቅራቢያ አካባቢ የእሳት እና ሌሎች አደጋዎች ቢከሰቱ ማህበረሰቡ በኮሚሽኑ አደጋ ጥሪ መቀበያ መስመሮች ፈጥኖ እንዲያሳውቅ ተጠይቋል።

#ማስታወሻ፥ ለእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች፣ ለወላድና የድንገተኛ ህክምና እና አምቡላንስአገልግሎትበነፃ መስመር 939፣ በቀጥታ መስመሮች 011155 53 00/011156 86 01 በመደወል ኮሚሽኑ ይገኛል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች