#Dangote
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

#Dangote
አሊኮ ዳንጎቴ በኬንያ 16 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ (East Africa Petroleum Refinery) ግንባታ አስጀመሩ።
የናይጄሪያው ቢሊየነር እና የአፍሪካ ቁጥር አንድ ባለሃብት አሊኮ ዳንጎቴ ከኬንያው ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር በመሆን በኬንያ ሰሜናዊ የባህር ጠረፍ ላሙ (Lamu) አካባቢ 16 ቢሊዮን ዶላር የሚፈጅ ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ።
በስነስርዓቱ ላይ ፦
- የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
- የአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ እና የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ
- የኡጋንዳ ፕሬዜዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ
- የቶጎ ፕሬዝዳንት ጂን-ሉክ ሳቪ ዴቶቭ
- የቤኒን ፕሬዝዳንት ሮማልድ ዋዳኝ ... እና ሌሎችም እንግዶች ተገኝተዋል።
የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካው ግንባታ ተጠናቆ ስራ ሲጀምር በቀን 700,000 በርሜል ድፍድፍ ዘይት የማጣራት አቅም ይኖረዋል። ይህ አቅም በምስራቅ አፍሪካ ትልቁ የኢንዱስትሪ ፕሮጀክት ያደርገዋል።
ፋብሪካው ከቀጣዩ ህዳር 1 ጀምሮ ግንባታው የሚጀመር ሲሆን በእቅዱ መሰረት በ2030 ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።
የፕሮጀክቱ አካል የሆነ 1,000 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው የኃይል ማመንጫ ጣቢያም ይገነባል ተብሏል።
ከዚሁ ፋብሪካ ጋር በተገናኘ አንዳንድ የአካባቢው ነዋሪዎች ለፋብሪካው በሚውለው መሬት ላይ የተሻለ ካሳ እንዲከፈላቸው በመጠየቅ ተቃውሞ እንዳላቸው ተነግሯል።
አሊኮ ዳንጎቴ እነዚህን ተቃውሞዎች " በአካባቢው ነጋዴዎች እና በዓለም አቀፍ አካላት የሚደረጉ ጨዋታዎች " ናቸው በማለት ውድቅ አድርገዋቸዋል። ፋብሪካው በታቀደለት ጊዜ እንደሚጠናቀቅ አጽንኦት ሰጥተዋል።
በሌላ በኩል እንደ "ሴቭ ላሙ" የሚባል ዘመቻ ቡድኖች ፋብሪካው በአካባቢው ማህበረሰብ እና ስነ-ምህዳር ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ተፅዕኖ አስመልክቶ የአካባቢ ጥበቃ ግምገማ ውጤቶች እንዲፋጠኑ ጠይቀዋል።
ሌላው ዳንጎቴ ለቀጣው መንግስታት በድምሩ 30 በመቶ ድርሻ ማቅረባቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ፋብሪካው በከፍተኛ የግንባታ ሂደት ወቅት እስከ 60,000 የሚደርሱ የስራ ዕድሎችን እንደሚፈጥር ተገልጿል።
ለምን ኬንያ ተመረጠች ?
ኬንያ ድፍድፍ ዘይት እንደማታወጣ በመጥቀስ ፋብሪካው እዛ እንዲሆን መመረጡ ላይ ጥያቄዎች ተነስተው ነበር። ለምሳሌ እነ ታንዛኒያ እና ዩጋንዳ እያሉ ለምን ኬንያ ተብሎ ነበር።
ይሁን እንጂ የኬንያ የኢነርጂ እና ፔትሮሊየም ሚንስትር ኦፒዮ ዋንዳይ እና አሊኮ ዳንጎቴ እንደገለጹት፣ ማጣሪያዎች ድፍስፍ ዘይትን ከዓለም አቀፍ ክፍት ገበያ የሚያገኙ በመሆኑ የሀገር ውስጥ ድፍድፍ ዘይት መኖር ግዴታ አይደለም።
ዳንጎቴ ሲንጋፖር አንድ ጠብታ ዘይት ሳታወጣ በርካታ ማጣሪያዎች እንዳሏት ለአብነት አንስተዋል።
ይህ የላሙ የነዳጅ ማጣሪያ ፕሮጀክት ከናይጄሪያ ውጭ በዳንጎቴ የሚከናወን ትልቁ ኢንቨስትመንት መሆኑ ታውቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 20 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia