#EthiopianAirlines🇪🇹
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

#EthiopianAirlines🇪🇹
ግዙፉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ረጅም ርቀት መጓዝ የሚችሉ አዳዲስ አውሮፕላኖች ግዢ እየተከናወነ መሆኑን አሳውቋል።
አየር መንገዱ ወደ አውስትራሊያ በረራ የመጀመር ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለውና ገበያውም እንዳለ መረዳቱን የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል።
ነገር ግን አሁን ላይ ወደ አውስትራልያ በረራ ለመጀመር " አውሮፕላን የለንም " ብለዋል።
ለዚህም ረጅም ርቀት መጓዝ የሚችሉ አዳዲስ አውሮፕላኖች ግዢ እየተከናወነ መሆኑን ተጠቁሟል።
አየር መንገዱ ከጥር 2020 ዓ.ም ጀምሮ ከቦይንግ እና ኤርባስ ኩባንያዎች የሚረከባቸው በርከት ያሉ አዳዲስ አውሮፕላኖች በመኖራቸው ለአውስትራሊያው መስመር በረራ መጀመር ዝግጅት እንደሚደረግ ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ሃምሌ 28 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia