#Mekelle
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

#Mekelle
ሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የትግራይ ሰላም ኃይል ወደ መሃል መቐለ ሮማናት አደባባይ መግባታቸው ተረጋግጧል።
መላው የከተማዋን ክፍል ሙሉ በሙሉ በቀጥጥራቸው ስር ማድረጋቸውም ተገልጿል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ፥ " የትግራይ ሰላም ለውጥ ምክር ቤት " አካል የሆነው የቃንጪ ሐቂ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ደጋፊ ጉድፈይ፣ " የመከላከያ እና የትግራይ ሰላም ኃይል (TPF) ጥምረት ብዙ ቦታዎችን ይዟል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ሀገር መከላከያ ከራያ አካባቢዎች ጀምሮ እስከ መቐለ ፣ ከሰቆጣ ጀምሮ እስከ ኮረምና አዲሸሁ፣ በአፋር ክልል በኩል አብዓላ ወረዳ እስከ መቐለ ያሉትን ቦታዎች እንደያዘ ገልጸዋል።
" በራያ አዘቦ እና ወጀራ በሚባለው አካባቢ ተቆርጠው የቀሩ የሕወሓት ታጣቂዎች ነበሩ እነርሱም ዛሬ ሌሊት ተሰባስበው እንደወጡ ነው ያለን መረጃ የሚያመላክተው " ሲሉ አክለዋል።
የሕወሓት አመራሮች መቐለን ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ በከተማው ከነትጥቃቸው የተበተኑ ታጣቂዎች ዝርፊያ ላይ ተሰማርተው እንደነበር ገልጸዋል።
ጦርነት በሚሆንበት ወቅት እየተከታተሉ የህዝብ ንብረት የሚዘርፉ እንዳሉ ገልጸው፣ " መከላከያ ሠራዊት ወደ አካባቢው በቶሎ መግባት ነበረበት። አሁን ገብቷል ሁኔታውን ያረጋጋል ብለን እናስባለን። 'ዘረፋ አለ' መባሉ ትክክል ነው " በማለት ገልጸዋል።
የቀድሞ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርና የአሁኑ የስምረት ፓርቲ አመራር ፕ/ር ክንደያ ገብረሕይወት " መቐለ ከኋላቀር ቡድኑ ነጻ ወጥታለች " ብለዋል። አሁን የተፈጠረው ሁኔታ ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑንም አመልክተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia