የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ የሂሳብ መዝገብ የማይዙ ግብር ከፋዮች የሚስተናገዱበትን የአሰራር ስርዓትን የሚዘረጋ ማስተናገጃ መመሪያ ይፋ አደረገ።
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ የሂሳብ መዝገብ የማይዙ ግብር ከፋዮች የሚስተናገዱበትን የአሰራር ስርዓትን የሚዘረጋ ማስተናገጃ መመሪያ ይፋ አደረገ።
• ይህ ሁሉን አቀፍ የማስተናገጃ አሰራር ተግባራዊ የሚሆነው ለ2018 የግብር ዘመን ብቻ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በ2018 የበጀት ዓመት የግብር ማሳወቂያ ወቅት የሂሳብ መዝገብ የማቅረብ ግዴታቸውን መወጣት ላልቻሉ የተወሰኑ የንግድና አገልግሎት ዘርፎች የተዘጋጀውን ዝርዝር የማስተናገጃ የአሰራር ስርዓት ይፋ አፍርጓል።
ቢሮው መስከረም 2019 ዓ.ም ባወጣው የክንውን መመሪያ እንዳብራራው፣ በተሻሻለው የፌዴራል ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 1395/2017 እንዲሁም በነባሮቹ አዋጆች ቁጥር 979/2008 እና 983/2008 መሰረት የደረጃ «ሀ» እና «ለ» ግብር ከፋዮች የሂሳብ መዝገብና መግለጫ መያዝ ህጋዊ ግዴታቸው ቢሆንም፣ በርካታ ከፋዮች የስራ ባህሪያቸውን ጠቅሰው ቅሬታ በማቅረባቸው ፍትሃዊ የታክስ አሰባሰብን ለማረጋገጥ የመጨረሻ የሽግግር አሰራር ዘርግቷል።
በመመሪያው ላይ በዝርዝር እንደተቀመጠው፣ ስራዎችን ከመንግስት ጋር በተገባ ውል ብቻ የሚያከናውኑ እና የተለየ ድጋፍ የሚሹ ግብር ከፋዮች ማለትም:-
- በትምህርት ቤቶችና በምግብ ማዕከላት ውስጥ በምግብ አቅራቢነት የተደራጁ መጋቢ እናቶች፣
- በከተማ ፅዳትና ውበት፣
- በደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብ እና በገፀ-ምድር ማስዋብ ላይ የተሰማሩ ማህበራት ከመንግስት ተቋማት የተከፈላቸውን ዓመታዊ ክፍያ የሚያሳይ ሰነድ ሲያቀርቡ፣ በደንብ ቁጥር 410/2009 ሠንጠረዥ «ሐ» መሠረት ግብራቸው ተሰልቶ እንዲከፍሉ ይደረጋል።
ከዚህም በተጨማሪ የሸገር ዳቦ የሚሸጡ ማህበራት በተጓዳኝ የሚያከናውኑት ተጨማሪ ንግድ መኖሩ በመስክ ምልከታ ከተረጋገጠ ተጨማሪው ስራ ብቻ ተለይቶ ግብር እንዲጣልበት ይደረጋል።
• የጫኝና አውራጅ፣
• የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ኤሌክትሪክ ምሰሶ ጉድጓድ ቆፋሪዎች፣
• በጥበቃ ስራ የተደራጁ ማህበራት እንዲሁም የታክሲ ታራ አስከባሪዎች የሂሳብ መዝገብ መያዝ ሲኖርባቸው ያልያዙ ግብር ከፋዮች ለዘርፉ በተቀመጠው የትርፍ ህዳግ መሰረት ግብራቸው ይሰላል።
በሌላ በኩል፣ የንግድ ስራ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሙያ ፈቃድ ብቻ አገልግሎት የሚሰጡ እንደ ጠበቆች፣ የኢንሹራንስ ወኪሎች፣ የኢንሹራንስ ጉዳት ገማቾች እና በአዋጁ የተዘረዘሩ ሌሎች 8ቱ ዘርፎች የሂሳብ መዝገብ ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ቢሆንም፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ወጪን በተመለከተ ዝርዝር መመሪያ እስካላወጣ ድረስ ቀደም ሲል በተጠኑ ጥናቶች መሰረት ከተገኘው አጠቃላይ ገቢ ላይ 35 በመቶው እንደ ወጪ እንዲያዝላቸው፣ ቀሪው 65 በመቶ ደግሞ ግብር የሚሰላበት የተጣራ ገቢ ሆኖ በሠንጠረዥ «ሐ» እንዲስተናገዱ ይደረጋል።
በግምት ግብር አዋሳኝ አዋጅ ቁጥር 138/2010 መሰረት የደረጃ «ሀ» የንግድና የመኖሪያ ኪራይ ገቢ ያላቸው አካላትም መዝገብ ካላቀረቡ በተመሳሳይ መልኩ 35 በመቶ ወጪ ተቀናሽ ተደርጎ በ65 በመቶ ገቢያቸው ላይ ግብሩ ይሰላል።
መመሪያው የትራንስፖርት ዘርፉን እና የአነስተኛ ግብር ከፋዮችን እድገት በተመለከተም ዝርዝር መፍትሔዎችን አስቀምጧል።
በትራንስፖርት ዘርፍ የተሰማሩ የደረጃ «ሀ» ግብር ከፋዮች በ2016 ወይም በ2017 የበጀት ዓመት የ57 በመቶ የዋጋ ግሽበት ማስተካከያ ተደርጎላቸው በደረጃ «ለ» ቀመር መሰረት ግብራቸውን እንዲያሳውቁ ይደረጋል።
በአዋጅ ቁጥር 979/2008 መሰረት በደረጃ «ለ» እና «ሐ» ስር ቆይተው በአዲሱ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ወደ ደረጃ «ሀ» ያደጉ ግብር ከፋዮችም የ2017 ዓመታዊ የንግድ ስራ ግብር እና የትርፍ ድርሻ ክፍያቸው ተወስዶ በደረጃ «ለ» አሰራር እንዲሰላ ተወስኗል።
በአዋጅ ቁጥር 1395/2017 አንቀጽ 23 አማራጭ አነስተኛ ግብር ለደረጃ «ሀ» ግብር ከፋዮች የተደነገገውም ከ2 ሚሊዮን ብር አማራጭ አነስተኛ ግብር 2.5 በመቶ ጋር ተነጻጽሮ የተሻለው ተወስዶ ግብር ይወሰናል።
ቢሮው በመሪሪያው ላይ እንዳመለከተው ፣ ይህ ሁሉን አቀፍ የማስተናገጃ አሰራር ተግባራዊ የሚሆነው ለ2018 የግብር ዘመን ብቻ ነው።
በዚህ እድል ተጠቃሚ የሚሆኑ ማናቸውም ግብር ከፋዮች ለቀጣዩ የበጀት ዓመት የሂሳብ መዝገብ ይዘው ለመቅረብ ህጋዊ የቃል-መሐላ እንዲፈፅሙ የሚደረግ ሲሆን፣ የሰነድ አለመያዝ አስተዳደራዊ ቅጣትም አብሮ ተግባራዊ እንደሚሆንባቸው ተመላክቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia