ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

#SaudiArabia🇸🇦

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
#SaudiArabia🇸🇦
#SaudiArabia🇸🇦

በሳዑዲ አረቢያ፣ የሰው ህይወት ያጠፋው ግለሰብ በሞት ተቀጣ።

የሳዑዲ ዓረቢያ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በመካ ክልል በግድያ ወንጀል ጥፋተኛ ተብሎ የሞት ፍርድ የተፈረደበት የየመን ዜጋ የሞት ቅጣቱ እንደተፈጸመበት አስታወቀ።

ዚያድ ዋሊድ መሐመድ አብዱላህ ሀይደራህ የተባለው ግለሰብ ከሌላ የየመን ዜጋ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት በሹል ነገር ጭንቅላቱን በመምታት ለሞት እንደዳረገው ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ጉዳዩ በፍርድ ቤት ታይቶ ጥፋተኛ መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ፣ ተከሳሽ ይግባኝ ቢጠይቅም የሞት ፍርዱ ጸንቷል። ይህንንም ተከትሎ በንጉሳዊ ትዕዛዝ የሞት ፍርዱ ትላንት ተፈጻሚ ሆኗል።

ሚኒስቴር እንዳለው፥ እርምጃው የሀገሪቱን ደህንነት ለማስጠበቅ፣ ፍትሕን ለማስከበር እና በሕይወት የመኖር መብት ላይ ሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመከላከል የሚወሰድ ሕጋዊ እርምጃ ነው።

ተመሳሳይ ወንጀል ለመፈጸም የሚያስቡ ሰዎችም በሕግ የተደነገገውን ከባድ ቅጣት እንደሚጋፈጡ ሚኒስቴሩ አስጠንቅቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች