#ጥንቃቄ⚠️
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

#ጥንቃቄ⚠️
" ሆዳቸው ተነፍቶ ከ200 በላይ ፍየሎች ናቸው የሞቱት " - አፋር ክልል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ
በአፋር ክልል ኪልበቲ ረሱ በበራህሌ ወረዳ ከዚህ ቀደም ተከስቶ በማያውቅ መልኩ በተመገቡት "የተመረዘ" ቁጥቋጦ አማካኝነት በርካታ ፍየሎች መሞታቸውን የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።
የቢሮድ ኃላፊ አቶ ሙሐመድ አሊ በሰጡን ቃል፣ "ሩኡራኢ የሚባል ቁጥቋጦ በልተው ሆዳቸው ተነፍቶ ከ200 በላይ ፍየሎች ናቸው የሞቱት" ብለዋል።
ይህንንም በአፋር ክልል የእንስሳት ሀብት እና ዓሳ ልማት ቢሮ የእንስሳት ጤና ጥበቃ፣ ቁጥጥርና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አብዱልቃድር ሙሐመድ (ዶ/ር) ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል።
አቶ ሙሐመድ፣ መሰል ነገር "ከዚህ በፊት አልተከሰተም፤ በተደጋጋሚ እንስሳት እየተከተቡ ስለሆነ ወርሽኝም አይደለም" ብለዋል።
በአንድ በኩል እንስሳቱ የሞቱት "በበሽታ" መሆኑ ተነግሮ የነበረ ሲሆን፣ በሌላ በኩል በአካቢው "የድንጋይ ናዳ" አጋጥሞ መሆኑን ሲገልጽ ቢስተዋልም፣ ኃላፊው ግን፣ " በሽታ ሆነ ናዳ ተከስቶ ሳይሆን ሩኡራኢ የሚባል አረንጓዴ ቁጥቋጦ ቅጠል በልተው ነው " በማለት ጉዳዩን አጣርተው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ይህን የቁጥቋጦ አይነት ተመግበው በዚህ መልኩ ከዚህ ቀደም የሞቱ እንስሳት እንደሌሉና እንዲህ አይነት ክስተት አጋጥሞ እንደማያውቅም ገልጸዋል።
አፋር ክልል የእንስሳት ምግብ ባለባቸው አካባቢዎች ተዘዋውረው ጭምር እንስሳትን በማርባት የሚተዳደሩ አርብቶ አደሮች የሚገኙበት ክልል ሲሆን ኃላፊው፣ ለእንስሳት ሞት ምክንያት ከሆነው ቁጥቋጦ እንዳይመገቡ ፍየሎቻቸውን እንዲጠብቁ ለነዋሪዎቹ መልዕክት አስተላልፈዋል።
" ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት። ህብረተሰባችን አርብቶ አደር ነው። የዛሬው ሞት የተከሰተው በኪልበቲ ረሱ በራህሌ ወረዳ ነው። በራህሌና አካባቢው ያሉት ይህንን ቁጥቋጦ እንዳይመገቡ ፍየሎቻቸውን መጠበቅ አለባቸው። የሞቱት ሞተዋል አይመለሱም ለቀጣይ ግን ጥንቃቄ ያስፈልጋል " ነው ያሉት።
እንስሳቱን ለሞት ዳረገ የተባለውን ተክሉን ማህበረሰቡ እንዲያጠፋ አስገንዝበዋል።
በክልሉ እንስሳት ሀብት እና ዓሳ ልማት ቢሮ የእንስሳት ጤና ጥበቃ፣ ቁጥጥር እና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶክተር አብዱልቃድር ሙሐመድ፣ እንስሳቱ የሞት አደጋ የደረሰባቸው በመርዛማ እጽዋት አማካኝነት መሆኑን ለአፋር ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
ተክሉ ድርቅ የማያጠቃው፣ ለሙቀት የማይመች መሆኑን አመልክተው ተጨማሪ ጥናት እንደሚደረግ ጠቁመዋል።
በራህሌ ወረዳውም ይህንኑ የዶክተሩን ገለጻ ያጋራ ሲሆን፣ እንስሳቱ የሞቱት በተመረዘ ተክል እንጅ በእንስሳት በሽታ እንዳልሆነም ገልጸዋል።
የበራህሌ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አሊ ሀሴን፣ 200 ፍየሎት ሲሞቱ፣ 500 የሚጠጉት እንደተጠቁ መግለጻቸው ተመልክቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia