ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

#UAE

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
#UAE
#UAE

" ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት፣ ለህዝቧ አንድነት፣ የግዛት አንድነት፣ ጸጥታ፣ ደህንነትና መረጋጋት የማያቋርጥ ድጋፍ እናደርጋለን " - የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች

የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች (ዩኤኢ) ህወሓት/TPLF እና ከእሱ ጋር የተባበሩ የታጠቁ ኃይሎች በኢትዮጵያ የፌዴራል ኃይሎች ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ገልጻ ድርጊቱን አወገዘች።

በተጨማሪም፣ ህወሓት በትግራይ የተለያዩ የአውሮፕላን ማረፊያዎችን መቆጣጠሩን እና በአጎራባች አፋር እና አማራ ክልሎች ወታደራዊ ግጭት መባባሱን አጥብቃ እንደምታወግዝ ይፋ አድርጋለች።

የዩኤኢ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ ሻክቡት ቢን ናህያን አል ናህያን፣ እነዚህ ክስተቶች የኢትዮጵያን አንድነት፣ ሉዓላዊነት እንዲሁም ጸጥታና መረጋጋት አደጋ ላይ የሚጥሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ ዩኤኢ ከኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ጎን ሙሉ በሙሉ እንደምትቆም ገልጸው፣ በኃይል ወይም በትጥቅ ትግል የኢትዮጵያን ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት ለመቀየር የሚደረግ ማንኛውንም ሙከራ እንደማትደግፍ ገልጻለች።

ዩኤኢ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት፣ ለህዝቧ አንድነት፣ የግዛት አንድነት፣ ጸጥታ፣ ደህንነትና መረጋጋት የማያቋርጥ ድጋፏን እንደምትሰጥ ሼክ ሻክቡት ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ በተጨማሪም ግጭቱ አስቸኳይ እንዲቆም እና የተባባሰው ውጥረት እንዲረግብ አሳስበዋል።

በተጨማሪም ሲቪል ሰዎችን መጠበቅ፣ ተጨማሪ ጥቃትና ግጭት እንዳይፈጠር መከላከል እንዲሁም የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነትን ማክበር አስፈላጊ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

ችግሮች በውይይትና በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ቅድሚያ መሰጠት እንዳለበትም ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ዩኤኢ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ለማረጋገጥ የሚደረጉ ጥረቶችን ሁሉ እንደምትደግፍ ሼክ ሻክቡት አረጋግጠዋል።

በተለይም የኢትዮጵያ ደህንነትና መረጋጋት እንዲጠበቅ እና በአፍሪካ ቀንድ ደህንነትን የሚያሰጋ ተጨማሪ ግጭት እንዳይፈጠር ጥረቶች እንደሚጠናከሩ አሳውቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች