" ... ወዴት እንሂድ ? ለማንስ አቤት እንበል ? " - አቶ ካሳሁን ፎሎ
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

" ... ወዴት እንሂድ ? ለማንስ አቤት እንበል ? " - አቶ ካሳሁን ፎሎ
የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን (ኢሠማኮ) በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳዮች ላይ ለሚያነሳቸው ጥያቄዎች ከአንዳንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ምላሽ እንደማያገኝ ገለጸ።
ኢሠመኮ እንደገለጸው፣ ለመንግሥት ተቋማት የሚጽፋቸው ደብዳቤዎች ምላሽ አያገኙም፤ ስልክ ሲደወልም ኃላፊዎች ስልካቸውን አያነሱም ፤ መልዕክት ሲላክም ምላሽ አይገኝም።
የኢሠማኮ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ እንደተናገሩት፣ ለሠራተኞችና ለአሠሪዎች ጉዳይ ምላሽ መስጠት የመንግሥት ተቋማት ኃላፊዎች ግዴታ ነው።
ነገር ግን አንዳንድ ባለስልጣናትና ኃላፊዎች ጉዳዮችን በእውነት፣ በመርህና በሕግ መሠረት ከመመለስ ይልቅ በራቸውን እንደሚዘጉ ገልጸዋል።
" ይሆናልም አይሆንምም አይሉም፤ ለመነጋገርም በፍጹም አይፈልጉም " ሲሉ አቶ ካሳሁን ተናግረዋል።
" ሁሉንም ነገር ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር መውሰድ አለብን ወይ ? " ሲሉም ጠይቀው፣ እያንዳንዱ መሥሪያ ቤት ለኢሠማኮ ብቻ ሳይሆን ለሚያቀርቡለት ማንኛውም ጉዳይ ለሌላውም ተገቢውን ምላሽ መስጠት እንዳለበት ገልጸዋል።
" የኢንዱስትሪ ሰላሙ እንዳይናጋ ወዴት እንሂድ ? ለማንስ አቤት እንበል ? " ሲሉም ጥያቄ አቅርበዋል።
ከመንግሥት ተቋማት በተለየ መልኩ የግል ተቋማት ኃላፊዎች ለኮንፌደሬሽኑ ጥያቄዎች ምላሽ እንደማይነፍጉ አቶ ካሳሁን ገልጸዋል።
ኢሠማኮ ምላሽና ማብራሪያ ለመስጠት የሚተባበሩ ጥቂት የመንግስት ተቋማትም እንዳሉ ጠቁሟል።
ከእነዚህም መካከል ፦
- የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፣
- የከንቲባ ጽሕፈት ቤት፣
- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጠቅሷል።
ኮንፌደሬሽኑ እንደሚለው፣ በአሠሪዎችና በሠራተኞች መካከል ጤናማ የሥራ ግንኙነት እንዲኖርና የኢንዱስትሪ ሰላም እንዳይናጋ፣ መንግሥታዊ ተቋማት ለሚያቀርብላቸው ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ መስጠት ይገባቸዋል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው። #ShegerFM
@tikvahethiopia