ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

" ለሕዝቧ ምቹ የሆነች፣ ለጠላቶቿ የማትንበረከክና በአለት ላይ የጸናች ሀገር ለመገንባት በአንድነት መሥራት ይገባል " - ሼይኸ መሀመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
" ለሕዝቧ ምቹ የሆነች፣ ለጠላቶቿ የማትንበረከክና በአለት ላይ የጸናች ሀገር ለመገንባት በአንድነት መሥራት ይገባል " - ሼይኸ መሀመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ
" ለሕዝቧ ምቹ የሆነች፣ ለጠላቶቿ የማትንበረከክና በአለት ላይ የጸናች ሀገር ለመገንባት በአንድነት መሥራት ይገባል " - ሼይኸ መሀመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ

‎የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ባለቤትና ሊቀ መንበር ሼይኸ መሀመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ " ኢትዮጵያ ከአደጉት የዓለም ሀገራት ተርታ እንድትሰለፍ ሚድሮክ  የበኩሉን አስተዋፅዖ በማድረግ ላይ ይገኛል " አሉ።

ይህን ያሉት ዛሬ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የቤተሰብ ቀን ሲከበር ነው።

በመርሃግብሩ ላይ በዙም የቀጥታ የቪዲዮ መልዕክት ያስተላለፉት የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ባለቤትና ሊቀመንበር ሼኽ መሀመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ " ምኞቴ ኢትዮጵን ከአደጉ ሀገራት ተርታ ተሰልፋ ማየት ነው " ብለዋል።

‎​ይህንን እውን ለማድረግ ሚድሮክ አሁን እየሰራቸው ካሉት የልማት ሥራዎች በተጨማሪ ባለ 10 ኮከብ ሆቴል በመገንባትና ሌሎች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁና ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ሥራዎች በመሥራት ተቋሙ ለሀገር ዕድገት የሚያበረክተውን አስተዋፅዖ የበለጠ ለማጉላት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

‎​በኢትዮጵያ የግሉና የመንግሥት ዘርፍ ተናበው በመሥራት የዋጋ ንረትን መከላከል እንዳለባቸው የጠቆሙት ሼይኸ መሀመድ፤ " ለሕዝቧ ምቹ የሆነች፣ ለጠላቶቿ የማትንበረከክና በአለት ላይ የጸናች ሀገር ለመገንባት በአንድነት መሥራት ይገባል " ሲሉ አሳስበዋል።

‎​ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ባለፉት ስድስት ዓመታት ያስመዘገበው ውጤት በጣም የሚያኮራ መሆኑን በመግለጽ ለተቋሙ ሠራተኞች እና አመራሮች ላከናወኑት ተግባር ምስጋና አቅርበዋል።

‎​በተለይም ሚድሮክ አሁን ላይ ከ80 ሺህ በላይ ሠራተኞች ያሉት መሆኑን ጠቁመው፣ ይህንን ቁጥር በእጥፍ ለማሳደግ መሥራት እንዳለበት አሳስበዋል።

‎​በተጨማሪም ሁሉም የሚድሮክ አመራርና ሠራተኛ የልማት ሠራዊት በመሆን ተቋሙ ቀጣይነት ያለው ዕድገት እንዲያስመዘግብ በባለቤትነት ስሜት እንዲሠራ ጥሪ አቅርበዋል።

Via ‎ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ

መስከረም 7 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች