" ሰዎች ተገድለዋል፤ ተፈናቅለዋል " - የኮልሜ ነዋሪዎች
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

" ሰዎች ተገድለዋል፤ ተፈናቅለዋል " - የኮልሜ ነዋሪዎች
👉 " የጤና እና ትምህርት ተቋማትን ጨምሮ 21 ቤቶች ተቃጥለዋል " - የኮልሜ ወረዳ አስተዳዳሪ
⚫️ " በእኛ ማህበረሰብ እንዲህ አይነት ድርጊት አልተፈጸመም። ነገር ግን ጣልቃ የገቡ አካላት አሉ " - የበና ፃማይ ወረዳ አስተዳዳሪ (ለዶቼ ቨለ ሬድዮ)
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከጳጉሜ 4 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ የኮንሶ፣ ኧሌ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች በሚዋሰኑባቸው አከባቢዎች ግጭት ተቀስቅሶ የሰው ህይወት ጠፍቷል፣ ንብረት ወድሟል፣ ሰዎች ተፈናቅለዋል።
ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ የኮልሜ ወረዳ ነዋሪ የሆኑ ሁለት አርሶ አደሮች፥ የነገሮች መነሻ ጳጉሜ 4/2018 ዓ/ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ገደማ መሆኑን ያመለክታሉ።
በዕለቱ ከበና ፀማይ ወረዳ የታጠቁ ሰዎች " ከብቶች ጠፍተውብናል ወደ ኮንሶ ዞን ኮልሜ ወረዳ መግባታቸውን በፋናቸው ተከታትለን መጥተናል " ብለው እንደገቡ ገልጸዋል።
የአከባቢው ሽማግሌዎችም ነገር ለማረጋጋት " እኛ እንፈልጋለን " ብለው እንደመለሷቸው አመልክተዋል።
በማግስቱ ጳጉሜ 5/2018 ዓ/ም ከማለዳው 12:30 ጀምሮ ግን ቁጥራቸውን በመጨመር ወደ ኮንሶ ዞን ኮልመ ወረዳ ማሶያ ቀበሌ በመግባት ጥቃት ማድረሳቸውን ነዋሪዎቹ ገልፀዋል።
ሌላ የማሶያ (ኩርጎ) ቀበሌ ማሶያ መንደር ነዋሪ ፥ " በጠዋት ድንገት ነው ተኩስ የተከፈተው ፣ ልጆችን ከእንቅልፍ ቀስቅሰን ነው የሸሸነው ሴቶችና ህፃናትን ካሸሸን በኋላ ወደ ሰፈር ስንመለስ ከብት፣ ፍየል፣ ዶሮ ሳይቀር ተዘርፎ ነው የጠበቀን " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ነዋሪዎቹ ምንም እንኳን አስቀድሞ ጥቃቱ የተፈጸመው ከበና ፀማይ በኩል በመጡ የታጠቁ ሰዎች ቢሆንም ኋላ ላይ ግጭቱን የሚፈልጉ ከኧሌ ዞን የተነሱ ታጣቂዎች ጥቃቱን መቀላቀላቸውን አሰረድተዋል።
በአጠቃላይ በኮንሶ በኩል የ6 ሰዎች ሕይወት መቅጠፉን ተናግረዋል። ቤቶች፣ እህል ፣ ጤና ኬላ (ማጎ ጤና ኬላ)፣ ወፍጮ ቤቶች እና የአምልኮ ስፍራ ሳይቀር በእሳት መውድመሙን አመልክተዋል።
ከኮልሜ ወረዳ በኩል ፦
- ኩርጎ፣
- ዱራይል፣
- ኪሲማና ቱካና ከተባሉ አካባቢዎች ከ5 መቶ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውንም አክለዋል።
አርሶና አርብቶ አደሮች በጋራ መስኖና እንስሳትን ለማጠጣት የሚጠቀሙበት የወይጦ ወንዝ በታጣቂዎች ቁጥጥር ስር መሆኑንም አመልክተዋል።
አሁን ላይ ሀገር መከላከያ መግባቱን፤ እስከ መስከረም 4/2019 ዓ/ም ከሰዓት ድረስ ተኩስ በአከባቢዎቹ እንደነበር ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ኃላፊዎች ምን ይላሉ ?
በኮንሶ ዞን የኮልሜ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፍቅሩ ብርሃኑ ስለ ጉዳዩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን ሰጥተዋል።
አስተዳዳሪው፤ ከጳጉሜ 3/2018 ዓ/ም ጀምሮ በደቡብ ኦሞ ዞን በና ፃመይ በኩል የ " ባላባት ከብት ጠፍቷል " በሚል አርሶ አደሮች ታጥቀው መምጣታቸውን ገልጸዋል።
በወቅትሙ በፀጥታ አካላት እንዲመለሱ ከተደረጉ በኋላ በማግስቱ በተደራጀ መልኩ በመምጣት ጥቃት መጀመራቸውን አመልክተዋል።
" ከዚህ ቀደም ለረጅም ዓመታት ግጭት ሲቀሰቅሱ የቆዩ አካላትም ከኧሌ በኩል ግጭቱን በመጀመር ቀበሌያትን ማቃጠል ማውደምና መዝረፍ ጀመሩ " ሲሉ ገልፀዋል።
እስካሁን በጥቃቱ 4 ሰዎች መሞታቸውን 6 ሰዎች መቁሰላቸውን ፤ የጤና እና ትምህርት ተቋማትን ጨምሮ 21 ቤቶች መቃጠላቸውን አስረድተዋል።
" አሁንም በተለይ በኧሌ ዞን ኮላንጎ ዙሪያ ወረዳ በኩል ከፍተኛ የጥፋት ዝግጅቶች አሉ " ያሉት አቶ ፍቅሩ ከፀጥታ አመራሮች ጋር በመሆን አከባቢዎቹን ለማረጋጋት እየተሰራ ስለመሆኑ ገልፀዋል።
የበናይ ፀማይ ወረዳ ምን አለ ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የበና ፃማይ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አይኬ ዞምቤን አነጋግራል።
" በፃመይ እና ኮንሶ ብሔረሰብ አዋሳኝ አከባቢ በከብት መጥፋት ምክንያት አለመግባባት ተከስቷል " ሲሉ ገልጸዋል።
ይህን ተከትሎ በበና ፃመይ በኩል 2 ሰዎች መሞታቸውና 3 ሰዎች መቁሰላቸውን ገልፀው አሁን በአከባቢው አንፃራዊ ሰላም መስፈኑን አመልክተዋል።
ከዚህ በተጨማሪ የወረዳው አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ዮሐንስ ጋሹ ለዶቼ ቨለ በሰጡት ቃል " በእኛ ማህበረሰብ እንዲህ አይነት ድርጊት አልተፈጸመም " ብለዋል።
" ነገር ግን ጣልቃ የገቡ አካላት አሉ ፡፡ ከዚህ በፊት ተፈናቅለው ወደ ወረዳው ከገቡ የአሌ ማህበረሰብ መካከል አንዳንዶቹ ጉዳዩን በዋናነት ያስተባበሩበት ሁኔታ አለ፡፡ አሁን ላይ ጥቃቱ መቆም እንዳለበት ከማህበረሰቡ ጋር እየተወያየን እንገኛለን " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia