በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሰው ሕይወት ማለፉና ከ2 ሺህ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸው ተገለጸ።
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሰው ሕይወት ማለፉና ከ2 ሺህ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸው ተገለጸ።
• የመሬት መንሸራተቱ አሁንም ድረስ በቦታው ላይ እየታየና እየተስፋፋ ነው ተብሏል።
በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ “ግልቤና” በተባለ ቀበሌ ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም በደረሰ ከባድ የመሬት መንሸራተት አደጋ የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉንና ከሁለት ሺህ በላይ ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሚመለከታቸው የወረዳው የሥራ ኃላፊዎች ሰምቷል።
እንደ ወረዳው መረጃ ከሆነ፣ በአደጋው ሳቢያ 411 አባወራዎች ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ሲሆን፣ ይህም በአጠቃላይ ከ2,000 በላይ የሚሆኑ የቤተሰብ አባላትን ለችግር ዳርጓል።
በአደጋው የአንድ ሰው ሕይወት ሲያልፍ፣ አራት ሰዎች ላይ ደግሞ መጠነኛና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል።
ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችም በወረዳው የጤና ተቋማት ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ታውቋል።
የመሬት መንሸራተቱ በንብረትና በእንስሳት ላይም ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።
እስካሁን ባለው መረጃ መሠረት 26 መኖሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ የተደረመሱ ሲሆን፣ 31 የቤት እንስሳትም በአደጋው መሞታቸው ተረጋግጧል።
የመሬት መንሸራተቱ አሁንም ድረስ በቦታው ላይ እየታየና እየተስፋፋ ቢሆንም፣ ማህበረሰቡ ቀድሞ አካባቢውን ለቆ ወደ ቀበሌው ማእከል እንዲወርድ በመደረጉ ተጨማሪ የሰው ሕይወት ጉዳት እንዳይደርስ መከላከል መቻሉን ወረዳው ገልጿል።
የአደጋው ሁኔታና የተጎጂዎች ዝርዝር መረጃ ተሰብስቦ ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት የተላከ ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ ለተፈናቀሉ ወገኖች የደረሰ ምንም ዓይነት አስቸኳይ እርዳታ አለመኖሩን ተነግሯል።
ተፈናቃዮቹ በአሁኑ ወቅት በቀበሌው ማእከል ተጠልለው የሚገኙ ሲሆን፣ አስቸኳይ የምግብና የቁሳቁስ እርዳታ እንደሚፈልጉም ተጠቁሟል።
ፎቶ፦ ፋይል
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia