ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

በትግራይ ክልል በ2018 ዓ.ም. 33 ሴቶች በግፍ መገደላቸው ተገለጸ።

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
በትግራይ ክልል በ2018 ዓ.ም. 33 ሴቶች በግፍ መገደላቸው ተገለጸ።
በትግራይ ክልል በ2018 ዓ.ም. 33 ሴቶች በግፍ መገደላቸው ተገለጸ።

እየተጠናቀቀ ባለው 2018 ዓ.ም. ብቻ በትግራይ 33 ሴቶች በግፍ መገደላቸውን የትግራይ ሴቶች ማህበር አስታወቀ።

ማህበሩ የተጎጂዎች ቤተሰቦች ፍትህ እንዲያገኙና የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

ይህ መረጃ የተሰማው በቅርቡ በመቐለ ከተማ የዘውዱ ሃፍቱ ግድያ ጉዳይ ላይ የተላለፈውን የፍርድ ቤት ውሳኔ በመቃወም የሴቶች መብት ተሟጋቾች እያካሄዱ ካሉት እንቅስቃሴዎች ጋር በተያያዘ ነው።

በመቐለ ከሁለት ዓመት በፊት በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደለችውን ዘውዱ ሃፍቱን ግድያ በተመለከተ፣ የመቐለ ማዕከላዊ ፍርድ ቤት ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. ተከሳሾቹ በነፃ እንዲለቀቁ ውሳኔ ሰጥቷል።

የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቃወም ዘጠኝ የሴቶች መብት ተሟጋች ሲቪል ማህበራት የጋራ መግለጫ አውጥተዋል። የመቐለ ዓቃቤ ሕግም የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ ማቅረቡ ታውቋል።

በተጨማሪም የዘውዱ ሃፍቱ ግድያ ጉዳይ ላይ የተላለፈው ውሳኔ " ኢ-ፍትሃዊ ነው " በሚል በርካታ ሴቶች የዘንድሮውን የአሸንዳ በዓል ጥቁር ልብስ በመልበስ ለማሰብ የሚጠይቅ እንቅስቃሴ ጀምረዋል።

ተሳታፊዎቹ ሙሉ ጥቁር ልብስ በመልበስ " የዘንድሮ የአሸንዳ አምባሳደር ዘውዲ ናት፤ ፍትህ በግፍ ለተገደለችው ዘውዲ " የሚሉ እና የሴቶች መብት እንዲከበር የሚጠይቁ መልዕክቶችን በማስተላለፍ ላይ ናቸው።

እንቅስቃሴው በተለይም በማህበራዊ ሚዲያ ገፆች በስፋት እየተሰራጨ ይገኛል።

የትግራይ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በበኩሉ እንቅስቃሴውን በመቃወም፣ የአሸንዳ በዓል ባህሉንና እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር የሚያስገነዝብ መግለጫ ቢያወጣም፣ የሴቶቹ የተቃውሞ እንቅስቃሴ በማህበራዊ ሚዲያ ቀጥሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች