ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

በአፋን ኦሮሞ ሙዚቃዎቿ የምትታወቀው አንጋፋዋ አርቲስት እልፍነሽ ቀኖ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች።

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
በአፋን ኦሮሞ ሙዚቃዎቿ የምትታወቀው አንጋፋዋ አርቲስት እልፍነሽ ቀኖ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች።
በአፋን ኦሮሞ ሙዚቃዎቿ የምትታወቀው አንጋፋዋ አርቲስት እልፍነሽ ቀኖ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች።

የኦሮሚያ ክልል " አርቲስት እልፍነሽ ለበርካታ ዓመታት በተለይም በትግል ዘፈኖቿና በግጥሞቿ ለኦሮሞ ሕዝብ መብት ስትታገል ቆይታለች " ብሏል።

" አርቲስቷ የጥበብን ኃይል በመጠቀም በሕዝባዊ ትግል ውስጥ ከፍተኛ ሚና በመጫወት በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ ድምጻውያን መካከል ናት " ሲል ገልጿል።

በምሥራቅ ወለጋ ዞን ነቀምቴ ከተማ አቅራቢያ በምትገኘው ሲቡ ጉቶ በተባለች ስፍራ የተወለደችው እልፍነሽ በ1969 ወደ ትግል በመቀላቀል ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በሥነ-ጥበብ ሥራዎቿ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክታለች።

ለበርካታ ዓመታት ከኖረችበት ኖርዌይ በቅርቡ ወደ ሀገሯ የተመለሰች ሲሆን፤ ባደረባት ሕመም በህክምና ስትረዳ ቆይታ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች፡፡

ጳጉሜን 1 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች