ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

"ወጣቶቻችን እና የሚቀጥለው ትውልድ በኢትዮጵያ ትልቁ ሀብት ውሃ ስለሆነ፣ የውሃ ልማቱን ይቀጥልበታል፣ ይገፋበታል ብለን እናስባለን " - ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
"ወጣቶቻችን እና የሚቀጥለው ትውልድ በኢትዮጵያ ትልቁ ሀብት ውሃ ስለሆነ፣ የውሃ ልማቱን ይቀጥልበታል፣ ይገፋበታል ብለን እናስባለን " - ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ
"ወጣቶቻችን እና የሚቀጥለው ትውልድ በኢትዮጵያ ትልቁ ሀብት ውሃ ስለሆነ፣ የውሃ ልማቱን ይቀጥልበታል፣ ይገፋበታል ብለን እናስባለን " - ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ፕሮፌሰር እና የቀድሞ የህዳሴ ግድብ ተደራዳሪ ቡድን አባል ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ ኢትዮጵያ ውሃዋን ማኔጅ እያደረገች ለራሷ እና ለጎረቤቶቿ ልታበቃ የምትችልበትን ትልቅ አቅም እያሳየች መሆኑን ገልጸዋል።

ከትላንት በስቲያ የኮይሻ የኃይል ማመንጫ ግድብ ለመጎብኘት በተገኙበት ወቅት ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር አጭር ቆይታ አድርገዋል።

ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ ምን አሉ ?

"የኮይሻ ግድብ ማለት ኢትዮጵያ ውስጥ እየተሰሩ ካሉት ትልልቅ ግድቦች አንዱ ነው። ጊቤ ላይ አራተኛው ነው። እንግዲህ በኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ግድቦች ለወደፊት ይሰራሉ።

እስካሁን ለተሰሩት ግድቦች፣ ይሄ አንዱ ማጎልበቻ ስለሆነ የኢትዮጵያን የመስራት አቅም፣ ሁለተኛ ኃይል የማመንጨት አቅም፣ ኢትዮጵያ ውሃዋን ማኔጅ እያደረገች ለራሷ እና ለጎረቤቶቿ ልታበቃ የምትችልበት ትልቅ አቅም ማሳያ ስለሆነ ዛሬ እዚህ በመገኘቴ በጣም ደስ ብሎኛል።

አሁን በጀመርነው፣ በያዝነው አጠቃቀም በጣም ጥሩ አጠቃቀም ነው። ህዳሴ ግድብ አሁን አልቆ ከተመረቀ ዓመት መሆኑ ነው፤ ከፍተኛ ኃይል እናመነጭበታለን። የኢትዮጵያን የኤሌክትሪክ ኃይል በ100 ፐርሰንት ጨምሮልናል።

ይሄ ደግሞ ሲጨመር፣ ምን ያህል እንደምጨምር እንገምታለን። ይሄ 1,800 ሜጋዋት ስለሆነ፣ ተጨማሪ ነው። እንግዲህ ይህንን የውሃ፣ በተለይም የግድብ ግንባታ በሌሎችም ጅረቶቻችን ላይ መቀጠል ያለብን ይመስለኛል።

ለኢትዮጵያ የግድብ ስራ እና የውሃ ልማት እነዚህ መጀመሪያዎች እና መነሻዎች፣ መማሪያዎች፣ አቅም መገንቢያዎች ናቸው። እንግዲህ ወጣቶቻችን እና የሚቀጥለው ትውልድ በኢትዮጵያ ትልቁ ሀብት ውሃ ስለሆነ፣ የውሃ ልማቱን ይቀጥልበታል፣ ይገፋበታል ብለን እናስባለን።

ይህ ለራሳችን ልማት ብቻ ሳይሆን፣ ጎረቤቶቻችንንም የምናስተሳስርበት ትልቁ አቅማችን ስለሆነ አሁን እስካሁን የተሰራው ስራ ብዙ አሳይቶናል፤ ኤሌክትሪክ እንሸጣለን ለሱዳን፣ ለጂቡቲ፣ ለኬንያ፣ ለታንዛኒያ፣ ለወደፊቱ ደግሞ ለሱማሊያ፣ ለሌሎችም የመሸጥ አቅማችን ከፍ እያለ ይሄዳል። በዚያው መጠን እነሱንም በጉርብትና እናስተሳስራቸዋለን ማለት ነው።

በዚያው መጠን የእኛ ከፍታ፣ የእኛ ተፅዕኖ በአካባቢያችን ከፍ ይላል፣ ዲፕሎማሲያችን ከፍ ይላል። እንግዲህ የውሃ ሀብታችን የሁሉም ነገር መሰረት ስለሆነ፣ አሁን ይሄ ትልቅ ማሳያ ነው፤ ለወደፊቱ እንቀጥልበታለን ብዬ ትልቅ እምነት አለኝ "
ሲሉ ነው የገለጹት።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ኮይሻ
ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች