በኮሬ ዞን በማሳቸው ላይ ሲሰሩ የነበሩ ሁለት አርሶ አደሮች በጥይት ተገደሉ።
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

በኮሬ ዞን በማሳቸው ላይ ሲሰሩ የነበሩ ሁለት አርሶ አደሮች በጥይት ተገደሉ።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን፣ ጎርካ ወረዳ ቆሬ ቀበሌ እና በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ሱሮ ባርጉዳ ወረዳ መካከል ባለው አዋሳኝ አካባቢ፣ በማሳቸው ላይ የእርሻ ሥራ ሲያከናውኑ የነበሩ ሁለት አርሶ አደሮች በጥይት ተገደሉ።
የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለጹት፣ አርሶ አደሮቹ በማሳቸው ላይ ሥራ ላይ እያሉ በተከፈተባቸው የጥይት ተኩስ ጥቃት ሕይወታቸውን አጥተዋል። ነዋሪዎቹ ከፍተኛ የተኩስ ድምፅ እንደሰሙና በኋላም ስለ አርሶ አደሮቹ መገደል መረጃ እንደደረሳቸው ተናግረዋል።
አርሶ አደሮቹ ተተኩሶባቸው ከተገደሉ በኋላ አስክሬን ለማንሳትም አስቸጋሪ ሁኔታ እንደነበር ነዋሪዎቹ አክለዋል።
ነዋሪዎቹ እንደሚሉት፣ በአካባቢው ከዚህ በፊትም አርሶ አደሮች በማሳቸው ላይ ሲሰሩ ጥቃት የሚደርስባቸው ሲሆን፣ ችግሩ ላለፉት 10 ዓመታት በመቀጠሉ የአካባቢው ነዋሪዎች በከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደሚኖሩ ገልጸዋል።
ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የዞኑ ከፍተኛ አመራር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል " አርሶ አደሩ ላለፉት 10 ዓመታት መውጫና መግቢያ መንገድ ተዘግቶበት በየጊዜው በማሳው ላይ መገደል የተለመደ ቢሆን ሀገራዊ ምክክር እየተደረገ ባለበት ወቅት ጭምር ይህ ጥቃት መፈጸሙ አሳዛኝ ነው፤ ችግሩ ምን ያክል ስር የሰደደ መሆኑንም ያሳያል " ብለዋል።
" ችግሩ ለረጅም ዓመታት የቀጠለና መንግሥት ዘላቂ መፍትሄ ያላበጀለት መከራ ነው " ሲሉ አስረድተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዞኑ የጸጥታና የፖለቲካ አመራሮች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ በወቅቱ አልተሳካም።
በሌላ በኩል፣ የኮሬ ዞን መንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ባወጣው መግለጫ፣ “ፀረ ሰላም” ብሎ በገለጻቸው ኃይሎች በተፈጸመ ጥቃት ሁለት ንጹሃን አርሶ አደሮች መገደላቸውን አረጋግጧል።
መምሪያው ከአጎራባች ዞኖች፣ ከክልሉ መንግሥትና ከሚመለከታቸው የጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በአካባቢው ዘላቂና አስተማማኝ ሰላም ለማስፈን እንደሚሰራ ገልጿል። የነዋሪዎችን ደህንነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ጥረቶችም እንደሚጠናከሩ አስታውቋል።
መምሪያው በተጨማሪም ህዝቡ በክስተቱ ሳይደናገጥ አካባቢውን በንቃት እየጠበቀ መደበኛ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴውን እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
ነሐሴ 9 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia