ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ አዲስ ስርዓተ ትምህርት (ካሪኩለም) ይፋ ማደረጉን ገለጸ።

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ አዲስ ስርዓተ ትምህርት (ካሪኩለም) ይፋ ማደረጉን ገለጸ።
የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ አዲስ ስርዓተ ትምህርት (ካሪኩለም) ይፋ ማደረጉን ገለጸ።

በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ከአሁን በፊት ከሦስተኛ ክፍል ይጀምር የነበረው ወደ ሰባተኛ ክፍል እንዲዘገይ ተደርጓል።

በተጨማሪም በቀድሞው ስርዓተ ትምህርት ያልነበረው የግብረ-ገብ ትምህርት በአዲሱ ካሪኩለም መካተቱን ቢሮው ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የትግራይ ትምህርት ቢሮ መረጃ፣ " በክልሉ ሲተገበር የቆየው ስርዓተ ትምህርት 16 ዓመታትን ያስቆጠረ " መሆኑን ገልፆ ፤ " ስርዓት ትምህርቱ የክልሉን ራዕይ ለማሳካት ከሚደረገው ጥረት ጋር በበቂ ሁኔታ የተጣጣመ አስተዋፅኦ አላበረከተም " ብሏል።

ቢሮው እንዳስታወቀው፣ የትምህርት ስርዓቱን ከዘመኑ ጋር ማጣጣም አስፈላጊ በመሆኑ፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተለወጠውን ዘመናዊ ዓለም የሚመጥን ስርዓተ ትምህርት መቅረፅ ወሳኝ ነው።

አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በ14 የዩኒቨርሲቲ ምሁራንና ባለሙያዎች መዘጋጀቱን ቢሮው ገልጿል። በስርዓተ ትምህርቱም ከአካባቢው ተሞክሮ በተጨማሪ ከእስያ የስነ-ምግባር ትምህርት፣ ከስካንዲኔቪያና ከሰሜንና ምዕራብ አውሮፓ ደግሞ እኩልነትና ተጠያቂነትን የሚመለከቱ ተሞክሮዎች መካተታቸውን አስታውቋል።

ቢሮው " አዲሱን ስርዓተ ትምህርት ለመቅረፅ ዩኒሴፍ 550 ሺህ ዶላር ፈቃድ ቢሰጥም፣ የፌዴራል መንግሥት በጀቱን ሙሉ በሙሉ ባለመልቀቁ እስካሁን ለስራው የዋለው 200 ሺህ ዶላር ብቻ ነው " ብሏል።

የ2019 ዓ.ም. የመማርና የማስተማር ሂደት በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት እንደሚከናወን የትምህርት ቢሮው አስታውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነሐሴ 9 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች