ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ትምህርት ሚኒስቴር በማስተማር ሥራ ላይ ያሉ መምህራንን ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና ለመጀመር በርካታ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ገልጿል።

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ትምህርት ሚኒስቴር በማስተማር ሥራ ላይ ያሉ መምህራንን ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና ለመጀመር በርካታ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ገልጿል።
ትምህርት ሚኒስቴር በማስተማር ሥራ ላይ ያሉ መምህራንን ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና ለመጀመር በርካታ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ገልጿል።

በቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ከአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ጋር የተናበበ የሥልጠና ማዕቀፍ፣ ፕሮግራሙን ለመምራት የሚያስችሉ የትግበራ ሰነዶችን እና የሰልጣኝ መምህራንን ምልመላ፣ መረጣ እና ምደባ መከናወኑን አመልክቷል።

ባለፉት አመታት በስልጠናው አሰጣጥ ጥራት ችግር ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የመምህራን የክረምት የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና በዚህ ክረምት ለማስጀመር 8 ዩኒቨርሲቲዎች ተለይተዋል።

እነዚህም፦
- ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ
- ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
- መቐለ ዩኒቨርሲቲ
- ጅማ ዩኒቨርሲቲ
- ሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ
- ጎንደር ዩኒቨርሲቲ
- አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሲሆኑ፣
በ2018 ዓ.ም. ክረምት 8,273 መምህራንን ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ወደ ስልጠና ለማስገባት ዝግጅት መጠናቀቁን ይፋ አድርጓል።

የመግቢያ ምዘና ወስደው ያለፉና በየዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ ሰልጣኝ መምህራን፣ ምዝገባው ሐምሌ 24 እና 25/2018 ዓ.ም. የሚካሄድ መሆን ትምህርት ሚኒስቴር አመልክቷል።

ሰልጣኞች በተጠቀሱት ቀናት በየተመደቡባቸው ዩኒቨርሲቲዎች በመገኘት እንዲመዘገቡ አሳስቧል።

ሰልጠኞች የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ ለማወቅ ይህን ሊንክ https://shorturl.at/ZjN9e መጠቀም ይችላሉ ተብሏል።

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች