#ኢትዮጵያ🇪🇹
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

#ኢትዮጵያ🇪🇹
ኢትዮጵያ ዛሬ የ2026 የአፍሪካ ሎጂስቲክስና ኮሙኒኬሽን ሲምፖዚየምን በአዲስ አበባ ማስተናገድ ጀምራለች። ሲምፖዚየሙ እስከ ሐምሌ 25 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን፣ ከ40 የአፍሪካ ሀገራት ተወካዮችና 26 ዓለም አቀፍ የኢንዱስትሪ ተቋማት ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።
የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሐመድ አዲስ አበባ አስተናጋጅ መሆኗ በኢትዮጵያና አሜሪካ መካከል ያለው የዲፕሎማሲና የወታደራዊ ትብብር ወደ ከፍተኛ ስትራቴጂያዊ ደረጃ መድረሱን የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል።
በአሜሪካ የአፍሪካ ዕዝ (AFRICOM) አዛዥ ጄኔራል ዳግላስ አንደርሰን በበኩላቸው፣ ሎጂስቲክስና ኮሙኒኬሽን ለዘመናዊ ወታደራዊ ተልዕኮዎች መሠረታዊ መሆናቸውን ገልጸው፣ የአፍሪካ ሀገራት ሽብርተኝነትንና ሌሎች የፀጥታ ችግሮችን ለመቋቋም በሎጂስቲክስ፣ በመረጃ ልውውጥና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ላይ ትብብራቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የሎጂስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል አብዱራህማን እስማኤል በበኩላቸው፣ ሲምፖዚየሙ የአፍሪካ ሀገራት ልምድ የሚለዋወጡበት፣ የጋራ የደህንነት አቅምን የሚያጠናክሩበት እና በሎጂስቲክስና በኮሙኒኬሽን ዘርፎች ትብብርን የሚያጎለብት ወሳኝ መድረክ መሆኑን ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀምሌ 20 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia